Connect with us

በግጥሙ አምባገነን ሥርዓት የጣለው ተወዳጅ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ

ቤተመንግስት በዜማው የማረከውና በግጥሙ አምባገነን ሥርዓት የጣለው ተወዳጅ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ
Photo: Facebook

ትንታኔ

በግጥሙ አምባገነን ሥርዓት የጣለው ተወዳጅ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ

ቤተመንግስት በዜማው የማረከውና በግጥሙ አምባገነን ሥርዓት የጣለው ተወዳጅ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ፡፡
***
ሀጫሉ ሁንዴሳ የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ ቢሆንም ሙዚቃን የዓለም ቋንቋ አድርጎ ከሰሜን እስከ ምዕራብ ከደቡብ እስከ ምስራቅ የተደመጠ ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሀጫሉን ሞት ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ግድያው ተራ ወንጀል እንዳልሆነና ሀገር ማበጣበጥ የፈለጉ የፈጸሙት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢት ህጓ ወይዘሮ አዳነች አበቤም ወንጀሉን የፈጸመው ማንም ይሁን ማን ከህግ እንደማያመልጥ በፌስ ቡክ ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ በዜማው የለውጥ ሃይሉን ለአራት ኪሎ ያበቃ ነው፡፡ በግጥሙ አምባገነን ስርዓት ጥሏል፡፡ ያመነበትን ፊት ለፊት በመናገርም ይታወቃል፡፡ ሁሉም ወገን ላይ የተሰማውንና የሚያምንበትን በመናገር እንጂ ጎራ ውስጥ በመግባትም ስሙ አይነሳም፡፡

የድምጻዊው አስክሬን በአሁኑ ሰዓት ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ በብዙሺህ ወጣቶች ታጅቦ እየተሸኘ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአርቲስቱን ሞት አስመልክቶ በጻፉት የሀዘን መግለጫ “ውድ ህይወት አጥተናል” ብለዋል፡፡ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁንና ታማኝ በየነም በታዋቂው አርቲስት አሰቃቂ ግድያ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ሀጫሉ ሁንዴሳ በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን የሰራ ተወዳጅ ድምጻዊና ታጋይ ነበር፡፡

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top