Connect with us

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የማይመለከታቸው ባለሥልጣኖችን ይሆን?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የማይመለከታቸው ባለሥልጣኖችን ይሆን?
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የማይመለከታቸው ባለሥልጣኖችን ይሆን?

ጎበዝ ኮሮና ከኢትዮጵያ ምድር ጠፍቷል ወይስ ሹማምንትን አይነካም? የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁስ ተሽሯል?

እርቀታችሁን አልጠበቃችሁም እየተባሉ የታሰሩ ሰዎች ጠቅላዩን ጨምሮ አዋጅ ያወጡት ሰዎች እንዲህ ተዛዝለው ሲያይ ምን ይሰማዋል?

እንዲህ ትከሻ ለትከሻ ገጥሞ ፎቶ ገጭ ከተቻለ፣ በየ አዳራሹ ምናምን ምረቃ እያሉ መሰባሰብ ከተቻለ ታዲያ ምርጫ ማካሄድ ምን ችግር አለው?

ብልጽግና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቶ ሲያበቃ እና የሌሎችን የመሰብሰብ መብት በአዋጁ ከጠረነፈ በኋላ የጦፈ የምርጫ ቅስቀሳ ውስጥ የተጠመደ ይመስላል።

በኮቪድ ዘመን፣ ከአራት ሰው በላይ በአንድ ቦታ አትሰባሰቡ ብሎ አዋጅ አውጥቶ ሲያበቃ፤ እየተንጋጉ ፋብሪካ ምረቃ፣ እየተንጋጉ ችግኝ ተከላ፣ እየተንጋጉ ፎቶ መነሳት የአዋጁን አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ ከመክተትም አልፎ ማህበረሰቡን ያዘናጋል።

ምርጫውም ከወዲሁ ፍትሃዊነቱ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። እድለኛ ከሆንን ሰላማዊና ስርቆት ወይም ማጭበርበር የሌለበት ምርጫ እናካሂድ ይሆናል። ፍትሃዊነቱ ግን ከወዲሁ ጭለማ እየዋጠው ይመስላል።

ያሬድ ኃይለማርያም
የመብት ተሟጋች

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top