Connect with us

አረቦች ኢትዮጵያ የህዳሴ ውሃ ሙሌትን እንድታዘገይ ጠየቁ

አረቦች ኢትዮጵያ የህዳሴ ውሃ ሙሌትን እንድታዘገይ ጠየቁ

ዜና

አረቦች ኢትዮጵያ የህዳሴ ውሃ ሙሌትን እንድታዘገይ ጠየቁ

ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ ወር ለሞሙላት የወጠነችው የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ዙሪያ የአረብ ሊግ የግብጽ አቋምን በመደገፍ መግለጫ አወጣ።

መቀመጫውን በካይሮ ግብጽ ያደረገው እና ሀያ ሁለት አባል አገራትን ያቀፈው ሊጉትናንት ባወጣው መግለጭው” ከወንዙ የታችኛው አገራት ከሱዳን እና ከግብጽ ጋር አግባቢ ስምምነት ሳይደርስ ኢትዮጵያ ውሃ የመሙላት ሂደቱን ልታዘገየው ይገባል”ሲል አሳስቧል።

በግብጽ አቤት ባይነት እና በኢንተርኔት /ቨርቹዋል/ አማካኝነት ለሊጉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተሮችየቀረበው ደብዳቤ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ በቀር “ሁሉም የሊጉ አገራት እሳት ሊያቀጣጥል ወደ ሚችል ጉዳይ እንዳይገቡ ” ሲል አስጠንቅቋል።

እንደ አርብ ሊግ ሁሉ ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄ ደብዳቤ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲሁ ሰኞ እለት ባወጣው መግለጫው “ሶስቱም አገራት ቁርቋሶን ወደ ጎን አድርገው ፣ በጋራ ሊሰሩ ይገባል” ማለቱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ያህ በእንዲህ እንዳለ የግብጽ የዲፕሎማሲያዊ ጦርነት ዘመቻ ያላስደሰታቸው የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአሶሴትድ ፕሬስ አርብ እለት በሰጡት አስተያየት”ጉዳዩ እዚህ መፍትሔ ሊያገኝ እየተቻለ እዚያ ድረስ (የተመድ)መውሰድ በአንድ ሉአላዊ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ያህል ነው” በማለት የግብጽ አቋምን ተችተዋል።

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top