Connect with us

አብን ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች …

አብን ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሄድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ ነው
Photo: Social Media

ፓለቲካ

አብን ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች …

አብን ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይካሄድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ ነው

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው የኮሮና ቫይረስ ስጋት መሆኑ ካቆመ ከዘጠኝ ወር በኋላ ይከናወናል ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚቀበለውና በህግ መንገድ እንደተካሄደ እንደሚያምን ገልጿል።

የንቅናቄው ምክትል ሊቀ መንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት “የአማራ ህዝብ ግዛቶች በነበሩትና በትግራይ ክልል አስተዳደር በማን አለብኝነት ያለአገባብ በተወሰዱት አካባቢዎች ማለትም በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በራያ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ምርጫ እንደምንወዳደር በማኒፌስቷችን አስቀምጠናል” ብለዋል።

ትግራይ ክልል ምርጫ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ በነዚህ ግዛቶች አሁን ሊደረግ የታቀደው ምርጫ እንዲታገድልን ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

በመሰረቱ የትግራይ ክልል የጀመረው የምርጫ እንቅስቃሴ ህገ መንግስታዊ እንዳልሆነ ቢታወቅም እኛ በተለይ ልንወዳደርባቸው የነበሩት ቦታዎች ላይ ምርጫው እንዳይደረግ እገዳ እንጠይቃለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“አንደኛ በማንኛውም በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስቱ መካከል ባለው የፖለቲካ ግንኙነት፤ በህወሀት መሩ ኢህአዴግ ማን አለብኝነት አማራን በመበደል ግዛቶቹ ተወስደው የተጠቃለሉበት ሂደት የድርድር አካል እንዲሆን አንፈልግም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ አካባቢዎች “የመታያ ፣ የጉቦ፣ ያንን ግዛት ሰጥቶ ሌላ ነገር የማግኛ የፖለቲካ መደራደሪያ እንዲያደርጉት እንደማንፈቅድ የትግራይ ክልል አስተዳደርም ፌደራል መንግስትም ሁለቱም አካላት እንዲያውቁት እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በነዚህ እኛ ልንወዳደርባቸው በነበሩት ቦታዎች ምርጫ እንዲታገድ ልንጠይቅ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“የፌደራል መንግስት ሲሆን ቶሎ የትግራይ ክልላዊ መንግስትን ህገ ወጥ እቅስቃሴ ማስቆም ነበረበት” ያሉ ሲሆን “የፌደራል መንግስት መሽኮርመሙን ማቆም አለበት፤ ህጉ የሚፈቅድለትም እርምጃ መውሰድ አለበት” ሲሉም ተናግረዋል፡

በትግራይ ክልል በርካታ ሰብአዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ነው፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ነው፤ በፌደራል መንግስት የማስቆም ስራም እየተሰራ አይደለም ፤ ብለዋል አቶ የሡፍ፡፡

ብልፅግና ከህወሀት ጋር ፍቺ እንኳን በቅርቡ እንዳከናወነ ያነሱት አቶ የሱፍ “ከዚህ ቀደም ጅምላ ግድያውንና ፣ማፈማቀሉን አይቶ እንዳላየ በማለፍ ሽፋን እንደሰጠው ሁሉ አሁንም ራቁት የወጣ የመብት ጥሰቱን ቁጭ ብሎ እንደታዛቢ ሆኖ ካለፈ በወሬ ደረጃ የሚለፈፈው ፣የኢትዮጵያ ቀጣይነትና ብልፅግና በርግጥ አሁን ነው አደጋ ላይ የሚወድቀው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መቋጫ በሌለው ተአቅቦ ዜጎች የማይተካ ዋጋ እየከፈሉ አይደለም ሀገረ መንግስትን የሚያረጋግጠው ያሉት አቶ የሱፍ የፌደራል መንግስት ብቻዬን ነኝ አይነት የተጋነነ የመነጠል ስሜት ካለው ከጎኑ ነን በሀገር ጉዳይ ድርድር የለንም፤ ቀላል ሀይል አይደለም ከጎኑ ያለው ፤ እንኳን እኛና የትግራይ ህዝብም ከጎኑ ነው ብለዋል።(ኢትዮ ኤፍኤም)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top