Connect with us

በሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የንግድ ቢሮ አስታወቀ

በሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ኢኮኖሚ

በሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የንግድ ቢሮ አስታወቀ

መንግስት ካስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ በላይ በሚሸጡ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና መመሪያውን አክብረው ለመስራት የተስማሙ የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮው አላስፈላጊ የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዳይዳከም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከፋብሪካዎች ተረክበው የሚሸጡ አከፋፋዮች የሚሸጡበት የአንድ ኩንታል ዋጋ እንደየርቀቱ ከ240.20 ብር እስከ 388.10 ብር እንዲሆን የተወሰነ ቢሆንም አንዳንድ አከፋፋዮች ግን ከተቀመጠው ዋጋ በላይ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ በተደረገ የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

መንግስት ባስቀመጠው የሲሚንቶ ዋጋ መሰረት ግብይት በማይፈጽሙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወሰድ ቢሮው ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሲሚንቶ ዝርዝር ዋጋ

Addis Ababa press secretary office

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top