Connect with us

ሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች  ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

ሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ህግና ስርዓት

ሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች  ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

ሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች  ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ሰበብ በማድረግ ሕገ-ወጥ የንግድ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሳሰበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የሀገሪቱን  ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት  በማድረግ በከተማዋ በምርት እና አገልግሎት ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ እጥረት እንዲፈጠር የተለያዩ  ምርቶችን  የሚደብቁ እና አከማችተው የተገኙ  ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም አጋጣሚውን በመጠቀም የመገልገያ ጊዜው ያለፈበትን ምርት ለገበያ የሚያቀርቡ፣ ምርት ላይ ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ የሚያቀርብ በጠቅላላው በሕገ-ወጥ ንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ነጋዴዎች ላይ ቢሮው ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን  ኃላፊው አስጠንቅቀዋል፡፡

ቢሮው ሕገ-ወጥ የንግድ ሥራን ለመቆጣጠር ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ግብረሃይል በማደራጀት ወደ ስራ ገብቷል ያሉት አቶ አብዱልፈታ ሸማቹ ሕብረተሰብም በከተማዋ በቂ አቅርቦት መኖሩን አውቆ ግብይቱን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከናውን ጠይቀዋል፡፡

ህብረተሰቡ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 8588 እና በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካል በማሳወቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቶ አብዱልፈታ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡(EBC)

 

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top