Connect with us

“ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን” – የሟች ቤተሰቦች

"ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን" - የሟች ቤተሰቦች
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

“ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን” – የሟች ቤተሰቦች

“ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን” – የሟች ቤተሰቦች

ግድያው ከተፈጸመ አንድ ዓመት የሞላው ቢሆንም ጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው የሚናገሩት የጀነራል ሰዓረ ባለቤት ኮሎኔል ጽጌ አለማየሁ፣ በማኅበራዊ ሚድያ ከሚሰሙት ውጪ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ይህ ጉዳይ ለእኔ ትልቅ ስቃይ ነው። ሰዓረ እና ገዛኢ ሕዝብ እያገለገሉ ነው በእሳት የተቃጠሉት፡፡ . . .[ገዳዩ] ተይዟል ይባላል። . . . በፍትህ ዙርያ ምን እየተሰራ እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም። ብዙ ሰው ይጠይቀኛል የማውቀው ነገር ግን የለም። ልባችን ጨልሟል፤ ቤታችን ጨልሟል” ይላሉ።

አክለውም “ሰዓረ፤ ጠበቃ እና ጠያቂ ያጣ ሰው ነው። የሚቆምለት ሰው የለውም፤ እኛ አቅም የለንም። ከእኔ አቅም በላይ ነው። ማን ጋር ተሂዶ አቤት እንደሚባልም አላውቅም፤ ጨንቆኛል” ይላሉ።

የሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ባለቤትም፣ “. . .ሰዓረ እና ገዛኢ ትልልቅ መሪዎች ናቸው። የአገሪቱ ጀነራሎች ናቸው። በሥራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት። የፌደራል መንግሥት፣ የመከላከያ እና ደኅንነት ባለበት አገር ትልልቅ መሪዎች ማን ገደላቸው? ለምን? መልስ ማግኘት ይገባን ነበር። ለቤተሰቡ ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን . . .” ይላሉ።

አክለውም “የማውቀውና ያነጋገረኝ ባለስልጣን የለም፤ እንደተጎዳን፣ ጥቃት እንደደረሰብን፣ ያን የመሰለ ሰው አጥተን በጭንቀትና በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ተረድቶ አይዟችሁ ያለን የለም፡፡ . . . የሚጠይቀኝ ባገኝ የሚሰማኝን እናገር ነበር. . . የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደን” በማለት ታጋይ አበባ ዘሚካኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል።(BBC)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top