Connect with us

ሱዳን የግብፅን ውሳኔ አወገዘች

ሱዳን የግብፅን ውሳኔ አወገዘች
Photo: Social Media

ዜና

ሱዳን የግብፅን ውሳኔ አወገዘች

ግብጽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በሂዴት ላይ እያለ ጉዳዩን ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን ሱዳን አወገዘች

ግብጽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በሂዴት ላይ እያለ ጉዳዩ ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን እንደማይቀበለው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኡመር ቀመርዲን ተናገሩ።

ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ አረበኛው እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት ብትጀምር ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት አትገባም።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ችግሩ በድፕሎማሲ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ሱዳን እንደምትሰራ መናገራቸውን መረጃው አስታውሷል።

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትን በሚቀጥለው ወር ለመጀመር የማንም ፈቃድ እንደማያስፈልጋት አስታውቃለች። በዚህ ክረምት የውሃ ሙሌቱን ለማስጀምር በሚያስችላት ዝግጅት ላይም ትገኛለች ።

ሰሞኑን ሶስቱ ሀገራት በግድቡ የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት ላይ አንዳች ስምምነት ላይ ለመድረስ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ለበርካታ ቀናት ሲደራደሩ የቆዩ ሲሆን፥ በመሰረታው የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን፥ ህግ ሆኖ ለመውጣት በሚያስችሉ የህግ ጉዳዮች ላይ ግን እንደሚቀራቸው ነበር የተገለፀው ።

በእስካሁኑ የድርድር ሂደት ላይ ሱዳን ተጨማሪ ምክር እንደምትፈለግ መግለጿን ተከትሎ ድርድሩ ከዚያ በኋላ እንደሚቀጥል በመስማማት ነበር የተለያዩት። ENA

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top