የቢል ጌትስ የኮቪድ-19 ክትባት ሌላው ገፅታ
(አምኃየስ ታደሰ | amhayest@gmail.com)
ይመለከቱናል ከምንላቸው እንደ አገራዊው ምርጫ ወይም ከወረርሽኙ ጋር የተያያዙ ትኩረታችንን የሳቡ ጉዳዮች ባልተናነሰ ራሱን የምድራችን ገዥ ያደረገው የቢል ጌትስ የፀረ-ወረርሽኝ ዘመቻ መዳረሻ ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ለበርካታ ዓመታት ደጋግሞ “መላው ዓለም ወደ ፊት ለሚገጥመን ወረርሽኝ አልተዘጋጀም” ሲለን የቆየው ነብዩ ቢል ጌትስ የፈለጋችሁትን ጠይቁኝ በተባለው የሬድኢት ማኀበራዊ መድረክ አማካይነት በቫይረሱ ምክንያት የተጣለው በነፃነት የመንቀሳቀስ ገደብ የሚነሳው “ማን ከበሽታው እንዳገገመ ወይም በቅርቡ ምርመራ እንደተደረገለት ክትባት ሲገኝ ደግሞ የተከተበውን ማወቅ የሚያስችል ዲጂታል መለያ ሲዘጋጅ” መሆኑን መግለጹ ችላ የማያሰኘው ሰውየው የሕክምና እውቀት ሳይኖረው በማያገባው ስለገባ ብቻ አይደለም፡፡
የቢል እና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን ኒው ዮርክ ውስጥ ኤቨንት-2ዐ1 በሚል መጠሪያ የምፅዓት ቀን ገጽታ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለማችን እንደተከሰተ አስመስሎ የመለማመድ መድረክ ዝግጅት ያስተባበረው የኮቪድ-19 ዜና ከቻይናዋ የውሃን ከተማ ከመሰማቱ ስምንት ሳምንታት አስቀድሞ ሲሆን ቢል ጌትስም አጠቃላይ ሃብቱ 1.44 ትሪሊዮን ከሆነው የማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን የቦርድ አባልነት ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ መላውን ጊዜውን እና ትኩረቱን በወረርሽኙ ዙርያ አድርጐ መንቀሳቀስ የጀመረው በአገረ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተነገረበት እለት ነበር፡፡
ይልቁንም ፋውንዴሽኑ ባለፉት 1ዐ ዓመታት ለክትባት ምርምር የመደበው የ1ዐ ቢሊዮን ዶላር “ድጋፍ” የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ጠብቆ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በመላው ዓለም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደተከሰተ የሚገልጸውን መግለጫ መስጠታቸው ድርጅታቸው ከጌትስ 50 ሚሊዮን ዶላር መቀበሉን መከተሉ የመገጣጠም ጉዳይ ካለመሆኑም በላይ እርሱም አጋጣሚውን ለክትባቱ ሲያፈስ የቆየውን መዋዐለ ንዋይ ለማስመለስ ብቻ እየተጠቀመበት አይመስልም፡፡
የገዛ ልጆቹን አስከትቦ እንደማያውቅ በቤተሰቡ ሃኪም የተረጋገጠው ቢል ጌትስ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ “መላው የምድራችን ነዋሪ ሊከተብ የግድ እንደሆነ” ማላዘኑ ከመነሻው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የምድራችን ነዋሪዎች እንደሚሞቱ የሚያመላክት ሪፖርት የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ እና የለንደን ኢምፔርያል ኮሌጅ እንዲሁም ለአሜሪኮው ብሄራዊ የጤና ተቋም እና የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል በድምሩ ከ2ዐዐ ሚሊዮን ዶላር በላይ በመለገስ በመላው አገራት መንግስታት ፈጽሞ በተጋነኑ እና በተሳሳቱ ትንበያዎች ሳቢያ ያልተጠበቁ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እና የሟቾቹ አሃዝ ቫይረሱ ያልተገኘባቸውን ሳይቀር እንዲያካትት በማድረግ እውነተኛ ወረርሽኝ እንደተከሰተ ለማስመሰል ሲደረግ የቆየው የጌትስ እና ግብረ አበሮቹ ጥረት ዘረፈ ብዙ እንደምታ ያለው ነው፡፡
የኘሬዝዳንት ትራምኘን መዋጮ ማቋረጥ ተከትሎ ለፀረ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዘመቻ ብቻ እስካሁን 35ዐ ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያደረገው ጌትስ ይልቁንም የተትረፈረፈውን ኃብታቸውን ደሴት ለመግዛት ከሚያውሉት ቢሊየነር መሰሎቹ በተቃራኒ በተለያዩ ጊዜያት በድምሩ 3.6 ቢሊዮን ዶላር በእርዳታ ስም በመስጠት የዓለም የጤና ድርጅትን በእጅ አዙር ሊቆጣጠር የበቃው ከሠብአዊነት በመነሳት ወይም ለበጐ አድራጐት ተግባራት ብቻ አይደለም፡፡
ለአብነትም ፋውንዴሽኑ ለድርጅቱ ከሰጠው ገንዘብ ውስጥ 6ዐ በመቶ የሚሆነው የልጅነት ልምሻን ለመከላከል ብቻ እንዲውል በፈጠረው ተፅእኖ የጤና ተቋሙ ከሩብ ያላነሰውን በጀት ለፖሊዮ ክትባት በመመደብ በአንፃሩ በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የድሆች አገራትን ዜጐች ላልተገባ ሕልፈተ ሕይወት የሚዳርጉት እንደ ወባ እና የሳንባ ነቀርሳ የመሳሰሉ መከላከል የሚቻል በሽታዎች እንዲዘነጉ ምክንያት ሆኗል፡፡
ቢል ጌትስ በገዛ ገንዘቡ የፈለገውን ቢያደርግ አይመለከተንም የማያሰኘው ደግሞ ግቡ የምድራችንን የጤና ስርአት ከመቆጣጠር መሆኑ ሲታሰብ ነው፡፡ በተለይም ጌትስ ያለውን ተሰሚነት ተጠቅሞ አይዲ 2ዐ2ዐ የሚባለውን የዲጂታል ክትባት ውጥን እውን ለማድረግ ከ4.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በመመደብ ከማይክሮሶፍት፣ ቢል እና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን፣ ኤክሴንቸር፣ ሮክፌለር ፋውንዴሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተውጣጣውን ጋቪ በተባለ የክትባት ጥምረት ተጠቅሞ በአውሮፓውያኑ 2ዐ3ዐ “ለሁሉም ሕጋዊ መለያ መስጠትን” ዓላማው ላደረገው የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት የሚደረገው ጥድፊያ አሉታዊ ተፅእኖዎች ጭምር እንደሚኖሩት አያጠራጥርም፡፡
በተጨማሪም ሾዲንገር በተባለ መድሃኒትን ከሶፍትዌር ጋር አቀናጅቶ በኮቪድ-19 ቫይረስ የክትባት ምርምር የተሰማራን ኩባንያ 3ዐ1 ሚሊዮን ዶላር አክሲዮን በቅርቡ የገዛው ቢል ጌትስ የኤምአይቲ ኘሮጀክት የሆነውን ኳንተም ዶት የተባለ በቆዳ ውስጥ ከክትባት ጋር የሚቀበር እና በልዩ የሞባይል ካሜራ የሚነበብ እንጂ በአይን የማይታይ ንቅሳት በፋውንዴሽኑ የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል ኃሳብ ያቀረበው “በማደግ ላይ ባሉት አገራት ማን የትኛውን ክትባት እንደወሰደ” ለመለየት መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ” መቀመጡም የሚያስነሳው የሰብአዊ መብት ጥሰት ይኖራል፡፡
ምክንያቱም በተለይም የድሆች አገራት ህፃናት “ከተወለዱ አንስቶ የሚገባቸውን መሠረታዊ መብቶች እና አገልግሎቶች ለማግኘት መከተባቸው” እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡ የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የናዚዎችን ወንጀል ለማየት የተሰየመው የኑረምበር የጦር ችሎት ኦሽዊትዝን በመሳሰሉ የማጐርያ ስፍራዎች የተፈጸሙት ከሕክምና ምርምር ጋር የተያያዙ ኢ-ሠብአዊ ድርጊቶች እንዳይደገሙ ብቻ ሳይሆን ሰዎች ጤንነታቸውን በሚመለከት ማንኛውም ጉዳይ ላይ በቅድሚያ በቂ መረጃ አግኝተው እና ፈቃዳቸውን መስጠታቸው ተረጋግጦ ሊወስኑ እንደሚገባ የሚደነግገውን የኑረምበርግ ኮድ የሚቃረን ነውና፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ለናይጄሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት 1ዐ ሚሊዮን ዶላር ጉቦ በመስጠት ከ2ዐዐ ሚሊዮን በሚበልጠው ሕዝቧ በሙሉ እንዲከተብ የሚያስገድድ ሕግ እንዲወጣ የማስደረግ ውጥን ያልተሳካለት ቢል ጌትስ በፋውንዴሽኑ አማካይነት የሚሰራጩት ክትባቶች በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ እንደ ሕንድ እና ቬትናም የመሳሰሉ አገራት ሕፃናት ላይ እያደረሱ ባሉት የማይቀለበስ ጉዳት የተነሳ በሕግ እስከመጠየቅ ቢደርስም በአገራችን ደግሞ “ለጤና አጠባበቅ ስርአቱ ባደረገው ወደር የለሽ አስተዋፅኦ” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ጨምሮ የተለየ ስፍራ ሊሰጠው በቅቷል፡፡
በመጨረሻም ቢል ጌትስ የዓለማችን ተቀዳሚ ባለ-ኃብት ከመሆን ይልቅ በ46.8 ቢሊዮን ዶላር ባለቤቱ እና አባቱ ጭምር በበላይነት የሚቆጣጠሩትን ፋውንዴሽን ያቋቋመው ከሠብአዊነት በመነሳት አለመሆኑን እና ብሉምበርግ በቅርቡ በ12 ወራት ውስጥ ለኮቪድ-19 ቫይረስ መከላከል ተግባር መዋል ይጀምራል ያለው እና ሚስቱ ሜሊንዳም ከታይም መጽሄት ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ “ተቀዳሚ ተጠቃሚዎቹ ጥቁሮች መሆናቸውን” የገለጸችው ክትባት ዓላማ ወረርሽኝ ከመከላከልም ያለፈ የመሆኑን ሃቅ በማስከተል ለማስረገጥ ቃል በመግባት ልሰናበት፡፡