Connect with us

ለእውነት ኑረን እንሙት!!

ለእውነት ኑረን እንሙት!!
Photo: Social Media

ፓለቲካ

ለእውነት ኑረን እንሙት!!

ለእውነት ኑረን እንሙት!!
(አለበል አማረ)

የሰኔ 15 / 2011 ዋና ዋና እውነታዎች
– እነ ዶ/ር አምባቸውን፣ እዘዝንና ምግባሩን ከአስር የማይበልጡና የሚታወቁ ወታደሮችን ይዞ የስብሰባ አዳራሻቸው ውስጥ በድንገት ገብቶ የገደላቸውና ያስገደላቸው ብ/ጀ አሳምነው ጽጌ ነው።/ በአይኔ በብረቱ ያየውት እውነታ ነው/

– የእነ ዶ/ ር አምባቸው ግድያ ከፌደራል መንግስት ጋር ለማያያዝ የሚደረገው ጥረት ፍጹም ውሸት ነው።

-የግድያ ወንጀሉን የመፈጸም ሃሳብና እቅድ የራሱ የአሳምነው መሆኑን አምናለሁ።

– አሳምነውን የባላሃብቶችና የአክቲቪስቶች ግፊት ነው ለዚህ ያበቃው የሚባለውን ሃሳብ ዋነኛ አድርጌ አልወስደውም።

የአሳምነውን የቆየ ባህሪ እና በወቅቱ የነበረውን ፍላጎት አወቀው ነበር፣ በወቅቱም አሳምነው እሱ ያሰበውንና የፈለገውን ብቻ የመፈጸም እንጅ የሌላ ሃሳብ የመስማትም ሆነ የመቀበል ባህሪ አልነበረውም።በርግጥ በተወሰኑ አክቲቪስቶችና ጥቂት ግለሰቦች

ስለ አሳምነውን ባልሆነ ሁኔታ የስም ግንባታ ላይ መጠመዳቸው ይታወሳል፣ ያን ግርግር እንደ ጉልበት አይቶታል ብየ አስባለሁ።

– አሳምነው ከክልሉ አመራር፣ ከአዴፓ አመራር፣ ከጸጥታ አመራሮችና ከዞን ሃላፊዎች ጋርም ተግባብቶ መስራት አልቻለም ነበር።

-እኔም ሆንኩ ሌሎች የጸጥታ አመራሮች በግልም በቡድንም ከሚመለከታቸው ጋር ተግባብቶ እንዲሰራ መክረነው ነበር፣ ግን ከሁላችንም ግንኙነቱን እያበላሸ ቀጠለ።

-መደበኛ የቢሮውንና እና የክልሉን የጸጥታ ስራ ከስሩ ያሉትን አስተባብሮ ከላይ ካሉት ጋር ተናቦ መስራት አቆመ፣ በሚመለከተው የጸጥታ የስብሰባ መድረኮች መገኘትም አቆመ።

-ሁላችንም በነበረው ሁኔታ ደስተኞች ስላልነበርን ቅድሚያ እሱን ለማሳመን ጥረት አደረግን፣ እንደማይሆን ስናውቅ ግን ለሚመለከታቸው የአዴፓ አመራሮች ችግሩን እንዲፈቱና እንዲያስተካክሉ ነግረናል። የፖለቲካ አመራሩ ይታዩ የነበሩትን ግልጽ አለመግባባቶችንና ችግሮችን ባለመፍታታቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብዬ አምናለሁ።

-አሁን ሶሻል ሚዲያ ላይ በተወሰነ ደረጃ እንደሚገለጸው የሌሎች ሴራ አለበት የሚባለው ዋናው ስራ የባለሙያ ቢሆንም ከአሳምነው ባህሪና በወቅቱ ከነበረበት ሁኔታ አንጻር ከራሱ ያለፈ ይሆናል ብዬ አላምንም።

– ሰኔ 12 አዲስ አበባ ላይ የነበረን የጸጥታ ግምገማ አስተማሪ ነበር፣ ብዙ መላላጥ የነበረ ቢሆንም መጨረሻ ግን እሱም የግምገማ ሃሳቡን ተቀብሎት ነበር፣ የሚቀጥለው ሰፋ ያለው የባህርዳሩ የጸጥታ መድረክም በአዲስ አበባው አይነት ሳይሆን የየአካባቢውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም የታሰበ ነበር።

– የግድያ እቅዱ / ሙከራው / ከባህርዳርም አልፎ ጎንደርና ወሎም ሙከራ ነበር።

-ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በወቅቱ በገፍ እያፈሱ የማሰሩ ድርጊት ተገቢ አልነበረም፣ አሁንም ያለ አግባብ የታሰሩ ስለመኖራቸው አምናለሁ።

በነዚህ እውነታዎች ላይ በመመስረት ቀጣይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በተለያዩ ሚዲያወች ይዠ እመለሳለሁ።
አላማዬ እውነታውን ህዝቡ እንዲያውቅና ካለፈው ስህተት ተፀፅተን ወደፊት መልካሙን እንድናይ ነው!!!

ከዚህ እውነታ በማፈንገጥ አሉባልታና በሬ ወለደ ውሸት በመፈብረክ የአማራን ህዝብ አንድነት ለመከፋፈል የሚደረገው ቁማር ማብቃት አለበት!!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top