Connect with us

የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ክልሉን በክብር ተረክቧል

የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ክልሉን በክብር ተረክቧል፡
Photo: Social Media

ፓለቲካ

የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ክልሉን በክብር ተረክቧል

27 ዓመት እርጥብ ሳር ይዞ ሲወጣ በጥይት እየተለቀመ በአምባገነኑ ኢህአዴግ መብቱ የተነፈገው ሲዳማ ክልልነቱን አረጋገጠ

የጥይት ድምጽ ሳይሰማ ክልሉን በክብር ተረክቧል | (ከትእግስቱ ማርዬ)

ዛሬ ሲዳማ ክልል ሆነ ሲባል የደቡብን ፖለቲካ ለልተከታተለ፣ ላላጤነና ብዙም ለማያውቀው ቀላልና እና እንዲሁ የተቸረ ይመስለዋል፡፡ ግን የዓመታት ትግል ውጤት ነው፡፡ ሲዳማ በቁጥርም በሀብትም በቆዳ ስፋትም አሁን ካሉት ከሦስቱ ክልሎች በቀረ ከሌላው የማንስበት ምክንያት የለም ብሎ ጥያቄ ያነሳው ገና በጠዋቱ ደቡብ ክልል በአቅጣጫ ሲጨፈለቅ ነው፡፡

ደቡብን በአቅጣጫ ጨፍልቆ በብሔር ብሔረሰቦች ራስን የማስተዳደርና መብት ላይ ጭቆናው ሲያርፍ እነ ዶክተር በየነ ጴጥሮስ ጭምር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን አንስተው ሥርዓቱ አፋኝና ብሔረሰቦችን ተጠቅሞ ብሔረሰቦችን የሚንቅ አስመሳይ መሆኑን ሞግተዋል፡፡

የሲዳማ እናቶች በንጉሡ ጉልበተኞችም ሆነ በወታደራዊው መንግስት በደል እንደ 1984 ዓ.ም. ደም አንብተው አያውቁም፡፡ ሲዳማ መብቱን ሲጠይቅ በባህሉ መሰረት ቅጠል ይዞ ነበር የወጣው መልሱ ግን ቀለሃና የጥይት ሀሩር ሆነ፡፡

ሃያ ሰባት አመታት በኢትዮጵያ ከተገፉ ብሔረሰቦች አንዱ ሲዳማ ነው፡፡ ሁሉንም እንካ ክልል ልሁን ካልክ ግን ትቀምሳለህ ተብሎ ጥርስ ውስጥ የገባ፡፡ ደቡብ ክልልን ለመምራት የመጀመሪያው መስፈርት ሲዳማን ማፈንና እንዲህ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ የማዕከላዊ መንግስቱ ተላላኪ ሆኖ መርገጥ ዋናው መስፈርት ነው፡፡

ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ወረዳ ልሁን ማለት ወንጀል ነበር፡፡ ዛሬ በልማት የሚጠቀሱት ስልጤዎች የማንነት ጥያቄያቸው እንዴት እንደተመለሰ ታሪካቸውን ጽፈው አኑረዋል፡፡ ዛሬም እንደ ቅማንትና ወለኔ ያሉት በማንነት ጥያቄ የገበቡት መከራ የሚታወቅ ነው፡፡

በትግራይ ሁለት ብሔር በአውራው ተጨፍልቋል፡፡ የሰገን አካባቢ ህዝቦች ቀላል የመዋቅር ጥያቄ በአምባገነኑ መንግስት ምላሹ የመቶዎች ግድያ አፈናና ለሁለት አመት መዋቅርን ማፍረስ ነበር፡፡ የቅማንቶች ስቃይ፣ የኮንሶዎች እንባና የሲዳማዎች ስቆቃ በመጨረሻም ሥርዓቱን አሽቀናጠረ፡፡

የደቡብ ፖለቲካ ድራማ ነበር፡፡ ሲዳማ ክልል መሆንን ላይመኝ ለዚህ ውለታው ክልሉን ሊመራ የክልሉ ብሔሮች ክልሉን መምራት ሲያምራቸው ሊቀር ባልሰለጠነ ፖለቲካ ተተብትቦ ኖሯል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከኢጣሊያ ወራሪ ሃይል በከፋ አበሳ ውስጥ ኖረው ዛሬ ደርሰዋል፡፡ የእነሱ የግንቦት ሃያ ፍሬ እከሌ የሚባለውን ሰውዬ ቤተ መንግስት ለተላላኪነት ማቅረብ ብቻ ነበር፡፡

ዛሬ ሲዳማ ክልል ሆኗል፡፡ ለውጡ አስቀድሞ ሲዳማ ክልል መሆን አይችልም የሚሉ ሲዳማ ሆነው ለማዕከላዊ መንግስት ለቀለብ ሲሉ የተቀጠሩ መሪዎቹን አስወገደ፡፡ ከዚያ በኋላ ቆራጥ መሪዎች ወደ ፊት አመጣና በመብቴ አልደራደርም የሚሉ ወጣቶች እምቢኝ ሲሉና አፋኙ ሥርዓት ሲንገዳገድ ነገሩ እንዳበቃለት ታመነ፡፡

ግንቦት 16 ቀን 1994 ሌላው ለሲዳማ ልዩ ቀን የምትባል የመስዋዕትነት ታሪክ የተመዘገባበት ዕለት ናት፡፡ በሐዋሳ ከተማ የተፈጸመውና ለዛሬ ድል ያበቃው ሌላው የመከራ ገፈት በዚህ ቀን ተፈጽሟል፡፡ በሐዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ሎቄ በሚባል ቦታ የሲዳማ ህዝብ ተጨፈጨፈ፡፡ በዚህ ቀን ከሰባ በላይ ንጹሃን ሞተዋል፣ የቆሰሉት የተጎዱትና ህይወትና ኖሮአቸው የተመሳቀለባቸውን ቤት ይቁጠራቸው፡፡

የሲዳማ ወጣቶች አጄቶ በሲዳማ ህዝብ ላይ በደል ሲያደርሱ ሲጨፈጭፉና ሲያሰቃዮ የኖሩ ወንጀለኞች በተደጋጋሚ ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲጠይቅ ቆጥቷል፡፡ መሪው በህይወት ባይኖሩም ትዕዛዙን ያስፈጸሙት ሳይጠየቁ ዋጋ የተከፈለበት መብት እውን ሆነ፡፡

ሲዳማ የፌውዳሉን ሥርዓት እንቢ ብሎ ለነጻነት የተዋደቀና የደርግንም ሥርዓት ለመጣል የታገለ ቢሆንም ከባዱ ትግል ግን በህገ መንግስት የተረጋገጠለትን መብት የተፈገበት የሃያ ሰባት አመት ትግል ነው፡፡

የሲዳማ እንዲህ ያለው የመብት ጥያቄ ለዘመናት የኖረ ቢሆንም በቀደሙ ሥርዓቶች ሊስተናገድበት የሚችልበት አግባብ አልነበረም፡፡ የቀደሙት ሥርዓቶችም በብሔር ብሔረሰብ መብት ስም የሚነግዱ ሳይሆኑ መልክ ያላቸው ጨፍላቂዎች ነበሩ፡፡ ሃያ ሰባት አመት ግን በህገ መንግስቱ የተቀመጠ መብቱን ለፈለገው ሲሰጥ ለፈለገው ሲነሳ ኖሮ አሁን ለድል በቅቷል፡፡

አምባገነኑ ሥርዓት መወገዱን ለማመን ዛሬ ብሔረሰቦች ህዳር ሃያ ዘጠኝ ብቻ በመጨፈር መብታችን ተከበረ ከሚሉበት ተቆርሶ የተሰጠ ፍላጎት ተላቀው ክልል መሆን መብታችን ነው ብለው መጠየቅ ነውር ያልሆነበት ዘመን ደርሰዋል፡፡ ከመጠየቅ ያለፈ መልስ መስጠት የጀመረው የለውጥ ሃይል አንድ ጥይት ሳይተኩስ የሲዳማ ክልልነትን ያረጋገጠ ውሳኔ በክልሉ ምክር ቤት አስረካቢነት በሲዳማ ህዝብ ተረካቢነት እውን ሆኗል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top