Connect with us

ማቆሚያ አልባው የብልጽግናና የህወሃት የማዶ ለማዶ ንትርክ

ማቆሚያ አልባው የብልጽግናና የህወሃት የማዶ ለማዶ ንትርክ

ፓለቲካ

ማቆሚያ አልባው የብልጽግናና የህወሃት የማዶ ለማዶ ንትርክ

አንዱ ኢህአዴግ እንደ አሜባ ሁለት ቦታ ተከፍሎ ዛሬም የኢትዮጵያ ሰላም እጦት ምክንያት ሆኗል፡፡
ማቆሚያ አልባው የብልጽግናና የህወሃት የማዶ ለማዶ ንትርክ፤
******
ከስናፍቅሽ አዲስ
ኢህአዴግ ተፈወሰም ታደሰም አበበም ጠወለገም ትርፉ ለኢትዮጵያ መከራ ነው፡፡ ዛሬም ከመከራ ያልወጣችው እዚህ በለጸግኩኝ እዚያ ደግሞ ወየንኩኝ ብለው አንድም ሁለትም በሚመስሉ አንድ ስሪቶች ነው፡፡

የኢህአዴግ ጠባይ ጉልበት፣ አምባገነንነትና አልሸነፍ ባይነት ነው፡፡ እንደ አሜባ ሲሰነጣጠቅ ደግሞ በየራሱ ይሄንን መንፈስ ይዞ ሄደ፡፡ ሁሉም አለቃ ሁሉም አቅሙን ማሳየት የሚፈልግ ሆነ፡፡ ዛሬም ሀገር እፎይ እላለሁ ስትል ደግሞ ሌላ ስጋት፤
ብልጽግና ተቆርጦ የሄደ ኢህአዴግ ነው፡፡ ህወሃትም እንደዚያው፡፡ አንዱን ከሌላው በንግግር እንጂ በግብር መለየት አቅቶናል፡፡

እርግጥ ነው ብልጽግና በአዲሱ የዳቦ ስሙ ነባር ያልሆኑ በዳዮችን አካቶ ሊሆን ይችላል፤ ነባር የሆኑ የበዳይነት ጠባዮቹን ግን ዛሬም አልተወም፡፡

ይሄኛው ኢህአዴግ በዚህች ሀገር ምርጫ አይኖርም ብሏል፡፡ ህግ አስደግፏል፡፡ በሙሉ ድምጽ አጸደቋል፡፡ ያኛውም ኢህአዴግ እንደዚሁ ምርጫ ህገ መንግስታዊ መብቴ ነው ብሏል፤ ህግ አስደግፏል፡፡ በሙሉ ድምጽ አጸድቋል፡፡

አዲስ አበባን 97 የምርጫ ድምጽዋን ቅርጥፍ አድርጎ ሲበላ ህግ አስደግፎ በሙሉ ድምጽ የራሱን እጅ አውጥቶ ነበር፡፡ አሁንም ማዶና ማዶ ሆነው በሙሉ ድምጽ የራሳቸውን እጅ አውጥተው የተለያየ ነገር ካልሆነ ብለዋል፡፡

ክፋቱ ከዚህ ቀደም አንድ ነበሩ፤ ሌላን ለማፈን ሌላን ለማንበርከክ ሌላን ለመጫን ነበር እንዲህ ዓይነት ህግ የሚያወጡት፤ አሁን ሁለት ናቸው፡፡ እንደ አሜባ ተበጣጥሰዋል፡፡ ሁለቱም ጉልበታቸውን ይታመናሉ፡፡ ሁለቱም ያልንው ካልሆነ የሚመጣው ይመጣል ይላሉ፤ ሁለቱም በየራሳቸው ሚዲያዎች ይጨፍራሉ፡፡ ሙዚቃው ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬም የሞት ዜማ ነው፡፡

የብልጽግናና የህወሃት የማዶ ለማዶ ክርክር በዚህች ዛሬም ከመከራ መውጣት ባልቻለች ሀገር ይዞ የሚመጣውን መገመት ነው፡፡ እነሱ ሌላውን አድምጠው ስለማያውቁ እርስ በእርስ ሊደማመጡ የሚችሉበት እድል የለም፡፡ ማንም ማንንም አይሰማም፡፡ ና ግጠመኝ ለማለት ጦርነት አያስፈልግም ብለው ይጀምራሉ፡፡ ያስፈልጋል የሚለውን አያስፈልግም በሚል ቃል የተኩ ባለቅኔዎች ናቸው፡፡

ለውጥ ሲሉ ተስፋ ያደረግነው ለእኛ ብለው ሳይሆን ለራሳቸው ሰላም ብለው ተለወጡ ብለን ነበር፡፡ በማግስቱ ሁለት ሆኑ፤ ከዚያ የጎራነት መንፈስ አቀነቀኑ ከዚያ በነገር ተጋጠሙ፤ አሁን በጉልበት ለመጋጠም “የማን አባት ገደል ገባ” እያሉ ነው፡፡

ይሄንን ሁሉ ላሰበ ኢህአዴግ ስሙ ማንም ይሁን ለኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ትርጉሙ ይገባዋል፡፡ ኢህአዴግ ሌላው ደርግ ነው፡፡ ስሙን የቀየረ ደርግ፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top