Connect with us

በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ

"በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ"
Photo: Social media

ጤና

በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ

“በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ”

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

ከሰሞኑ ጤና ሚንስቴር የሚሰጠው የኮቪድ-19 መግለጫ ላይ “በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ” የሚል አዘውትረን እየተመለከትን ነው ፤ ይህ ጉዳይ ህብረተሰቡ ላይ ጥያቄን ፈጥሯል።

በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ ማለት:-

1. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ምርመራ ሳይደረግ የኮሮና ተጠቂ ሆኖ የህልፈቱ ምክንያት ኮሮና ቫይረስ ሲሆን፣

2. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ምርመራ ሳይደረግ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሆኖ ተጓዳኝ በሽታ ሲኖርበት፣

3. ሟች ህይወቱ ከማለፉ በፊት ናሙና ሰጥቶ ዉጤቱ ሳይደርስ ህይወቱ ሲያልፍ፣

ታድያ አስከሬን መመርመር ለምን አስፈለገ ?

ለዚህ ጥያቄ መልስ ሊሆነን የሚችለው የሞቱን ምክንያት ለማወቅ እና በኮሮና ቫይረስ ከሆነ ንክኪ እና ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች ለመለየት ነው።

‘ሟች ቫይረሱን ከየት አመጣው ?’ የሚል ጥያቄ ያስነሳ ይሆናል ፤ ነገር ግን ባሁኑ ሰዓት ሁሉም ሰው ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ስለሆነ በየትኛውም ቦታ እና ከማንኛውም ሰው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ሊይዘን ስለሚችል ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top