Connect with us

ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃ ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃ ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
Photo: Social media

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃ ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ያመጠቀቻት ሳተላይት የምትልከውን መረጃ ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል
በአሁን ላይ የሳተላይት ቁጥጥር ስራው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን እየተካሄደ ነው

ኢትዮጵያ ያመጠቀቻት የመሬት መመልከቻ ሳተላይት (ETRSS-1) የምታመጣውን መረጃ ለሚፈልጉ አካላት ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም በቻይናውያን ሲከወን የቆየው የሳተላይት ቁጥጥር ስራ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እየተካሄደ ነው።

ጥሩ የእዉቀት ሽግግር በመደረጉ ስራው በኢትዮጵያዊያን አቅም መካሄድ መጀመሩንም ተናግረው፤ የኢትዮጵያውያኑን ዓቅም ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ሳተላይቷ መረጃ መላክ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ ያለማቋረጥ እየተሰበሰበ ነው።

ኢትዮጵያ ሳተላይቷን በማምጠቅ መረጃ ለማግኘት የምታወጣውን ወጪ ከማስቀረት ባለፈ መረጃ በመሸጥ ገቢ ማግኘት መጀመሯን የገለጹት ዶክተር ሰለሞን፤ ሳተላይቷ የምታመጣውን መረጃ ለሚፈልጉ አካላት ለመሸጥ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል።

የምስል ግዢ ፍላጎት ላቀረቡ አገሮች ምላሽ መስጠት እንደተጀመረም ዶክተር ሰለሞን አስረድተዋል።
አሰራሩን ቀላል ለማድረግ ጥረት መደረጉንም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪዋን የመሬት መመልከቻ 72 ኪሎ ግራም የምትመዝን ‘ETRSS-1’ ተሰኘችውን ሳተላይት ወደ ህዋ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ማምጠቋ ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top