Connect with us

ምክትል ኢታማዧር ሹሙ የግብፅ መሪዎችን ገሰፁ

ምክትል ኢታማዧር ሹሙ የግብፅ መሪዎችን ገሰፁ
Photo: EPA

ዜና

ምክትል ኢታማዧር ሹሙ የግብፅ መሪዎችን ገሰፁ

“የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ግብጽ ዓለምም ያውቃል”

የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ግብጽ ዓለም እንደሚያውቀው የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ። የተሳሳተ የመሪዎቿ አስተሳሰብ ግብጽን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳትም አመልክተዋል።

ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት ግብጾች ኢትዮጵያዊያን ጦርነት ከመጣ እንዴት ጦርነትን መሥራት እንደሚችሉ በሚገባ ያውቁታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለችም ግብጽ ዓለም ያውቃል። በሀገሩ ጥቅምና ሕልውና የሚደራደር ኢትዮጵያዊ የለም።

የጦር መሣሪያ በገፍ መሰብሰብ ብቻ በጦርነት ውስጥ ለድል አያበቃም ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በጦርነት ውስጥ ለድል የሚያበቁ ሳይንሳዊ የሆኑ የጦርነት መሰረታውያን የሚባሉ ሕጎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ጀነራል ብርሃኑ እንዳሉት ለድል የሚያበቁት የመሰረታውያኑ ቁልፎች በሙሉ በኢትዮጵያውያን እጅ ናቸው፤ ግብጾች 30 እና 40 ዓመት ሙሉ የሰበሰቡት ብዙ አይነት የጦር መሣሪያ አላቸው፤ በዚህ አስፈራርተው የጋራ የሆነውን ውሃ እንዳትነኩ ለማለት ይሞክራሉ። መሪዎቿ በዚህ መልኩ ማሰብ አልነበረባቸውም።

ግብጻዊያን ከኢትዮጵያ ጋር በጭራሽ መጣላት ሳይሆን ኢትዮጵያንን ተንከባክበው በመያዝ ውሃውን እንዴት አድርገን በጋራ እንጠቀም ማለት ነበረባቸው ያሉት ጀነራሉ፣ ፈጣሪ ውሃውን ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጠረው፤ ወደ ሱዳንና ግብጽ እንዲፈስ አደረገው፤ የወንዙ ውሃ ኢትዮጵያ፤ ሱዳን፤ ግብጽም ላይ ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል። ከዚህ ባለፈ ከላይ ያለው ሀገር እንጂ ከታች ያለው ሀገር ውሃውን መጠቀም አይችልም የሚለው እሳቤ አያስኬድም፣ የዓለም ሕግም አይደግፈውም፤ ይሄ የተሳሳተ የመሪዎቿ አስተሳሰብ ግብጽን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳታል ብለዋል ።

“ግብጽ አሁን የያዘችው መንገድ ለሀገሪቱ ብዙ ጠላት የሚያፈራባት ነው፤ ጠላትነት በጨመረ ቁጥር ጭራሹንም ውሃው ሙሉ በሙሉ የእኔ ነው ወደሚል የእልህ መንገድ ይወስዳል” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹሙ፣ መቼም ቢሆን የግብጽ ሠራዊት ኢትዮጵያ ገብቶ ምሽግ ሠርቶ የዓባይን ገባር ወንዞች አይጠብቅም፤ የኢትዮጵያን ምድርንም አይረግጥም፤ እነዚህ ወንዞቻችን ከጦርነትም በላይ ታላቅ አቅምና ጉልበት አላቸው ብለዋል።

#ኢፕድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top