የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር በፓርላማ አባሉ ዕይታ
(ተስፋዬ ዳባ የፓርላማ አባል)
የጠቅላይ ሚንስትራችን የፓርላማ ውሎ በትግራይ ህዝብ የነበረ ብዥታ መስመር ያስያዘ እና ቀጣይም በትግራይ ተጨማሪ መሰረተ ልማቶች ለመስራት በፌደራል መንግስት በዕቅድ መያዙን ያረጋገጠ ነዉ ። የምንወደውን የትግራይ ህዝብ አትወዱትም ጎዳችሁት የሚለን ካለ አቧራ ነው ያልፋል፤ አሻራው ይገለጣል፤ ያኔ ህዝቡ እውነታውን ይረዳል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ክቡር ጠቀላይ ሚንስትሩ ከመቼዉም ጊዜ በላቀ የተሳካ እና በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ በተለይ ደግሞ በትግራይ ህዝብ የነበረ ብዥታ መስመር ያስያዘ እና ቅቡልነት ያገኘ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚንስትራችን ሲጀመር ጀምሮ ለትግራይ ህዝብ ያላቸው በጎ አሳቢነት ፍንትው አድርጎ ያሳየ ንግግር ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚንስትራችን የትግራይ ህዝብ ጠላት ናቸው እየተባለ እስካሁን ድረስ ሲሰበክ የነበረው ሁሉ እንደ አቧራ በንኖ እንዲጠፋ ያደረገ ቀን ነበር፡። ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ፓርቲያቸው ብልፅግና በሚመሩት ፌደራል መንግስት ለትግራይ ህዝብ ካላቸው ቅን እሳቤ ተነስተው እስካሁን ድረስ የትግራይ ህዝብ ሳይሰማ ከሰርዋቸው በርካታ መሰረተ ልማቶች:-
❶-የትግራይ ክልል መንግስት የትግራይ ገበሬ የማዳበርያ እዳ ከነ ወለዱ አንቆ የተቀበለ መሆኑ መላው የትግራይ ህዝብ በተለይ ገበሬው የሚመሰክረው ሃቅ ነው፡፡ነገር ግን የትግራይ መንግስት ከገበሬው የሰበሰበው የማዳበርያ እዳ ለፌደራል መንግስት ገቢ እንዳላደረገ በይፋ ሰምተናል፡፡ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትራችን እና መንግስታቸው ለትግራይ ህዝብ እና ገበሬ ካላቸው ቅን አመለካከት ተጨማሪ 445 ሚልዮን ብር ከፌደራል ካዝና ተበጅቶ ማዳበርያ ተገዝቶ እንዲላክልን አድርገዋል፡፡
❷-ባለፋት 20 አመታት የመቀሌ ህዝብ በቂ የውሃ አቅርቦት ባለ ማግኘቱ ሲሰቃይ እና ሰሚ አጥቶ እንደ ኖረ አደለም የመቀሌ ህዝብ ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመሩት የለውጥ ሀይሉ ብልፅግና ፓርቲ ወደ ስልጣን እንደ ወጣ የመጀመርያ እርምጃው ለመቀሌ ህዝብ በቂ እና ንፁህ ውሃ ማቅረብ የሚችል ብቸኛው እና ትልቁ ግድብ ገረብ ግባ እንዲሰራልን የ 8 ቢልዮን ብር በጀት እንዲፀድቅ በማድረግ በፍጥነት እንዲጀመር ደግሞ 1.3 ቢልዮን ብር ከፌደራል መንግስታቸው በጀት በፍጥነት እንዲለቀቅልን አድርገዋል፡፡መላው የመቀሌ ህዝብ በየቤቱ ደስታውን እየገለፀ ይገኛል፡፡
❸-ለኮረና ቫይረስ መከላከያ 45 ሚልዮን ጥሬ ገንዘብ እና በጣም በርከት ያለ የኮሮና ቫይረስ ለመመርመር እና ለመከላከል የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችም ጭምር ፌደራል መንግስት ለትግራይ ህዝብ እንደ ሰጠ በህዝብ ተወካዮች ፊት በይፋ ሀቁ ተነግሮናል፡፡
❹- ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል 23 የመንገድ እና የውሃ ፕሮጀክቶች ቢልየኖች በጅቶ እየሰራ እንደ ሆነ በህዝብ ተወካዮች ፊት እውነቱ ተነግሮናል፡፡
❺-ቀጣይም በትግራይ ብዙ ተጨማሪ መሰረተ ልማቶች በፌደራል መንግስት እንደ ሚሰሩ የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስተራችን ቃል ገብተውልናል፡፡
❻-ከትግራይ ህዝብ አብራክ የወጡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም፡እኩልነት እና ዲሞክረሲ ብለው በ 10 ሺዎች መስዋእት የከፈሉ በ 100 ሺዎች ኣካላቸው የጎደሉትንም በማመስገን ያላቸው ክብር በይፋ በተወካዮች ምክር ቤት ሀቁ ነግረውናል፡፡
❼-ላለፉት አመታት በአባይ ግድብ ተደቅነው የነበሩ ጎታች ፈተናዎች በመለየት እና መስመር በማስያዝ ለስኬት እየደረሰ መሆኑ በይፋ አበስረውናል፡፡
የትግራይ ህዝብ ጀግናና በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ጥሮ ግሮ የሚበላ ህዝብ ነው፤ ይሄ የሚካድ ሀቅ አይደለም፤
የትግራይ ክልል መንግስትን በሙሉ ሌባ፣ አጥፊ፣ የማይሰራ አድርጎ ማሰብ ስህተት ነው፤ ኢትዮጵያን የሚወዱ ክልሉን ለመለወጥ የሚጥሩ ብዙ ሰዎች በመሀሉ አሉ፤
ህወሓትን ከሊቀመንበሩ ጀምሮ ሁሉም ጥፋተኛ ናቸው የሚል እምነት የለንም፤ በፓርቲው ውስጥ ለዚህ አገርን ህዝብ መስዋዕትነት የከፈሉ ባለውለታዎች አሉ፤ ይሄ ማለት ጥፋተኛ፣ የሚሳደቡ፣ ወንጀለኛ በመሃላቸው የለም ማለት አይደለም፤
ትግራይ እስከ ለውጡ ድረስ በጀቱ ማደግ የቻለው 7 ቢሊዮን ብር ድረስ ነው፤ ከለውጡ በኋላ የተመደበለት በጀት ግን 42 በመቶ አድጓል፤ ይሄ እድገት ለፕሮጀክት የሚመደብን ገንዘብ አይጨምርም፤ የትግራይን ህዝብ የመጉዳት ዜሮ በመቶ ፍላጎት የለንም ።
የምንወደውን የትግራይ ህዝብ አትወዱትም ጎዳችሁት የሚለን ካለ አቧራ ነው ያልፋል፤ አሻራው ይገለጣል፤ ያኔ ህዝቡ እውነታውን ይረዳል።
ባጠቃላይ በጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር በኢትዮጵያ ህዝቦች በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ህዝብ የነበረው ውዥንብር ፍንትው አድርጎ የጠራ መስመር ያስያዘ ነበር፡፡