Connect with us

‹‹ያዝ እጅዋን፣ ዝጋ ደጅዋን›› እያለ የሚዘፍን ማህበረሰብ …

‹‹ያዝ እጅዋን፣ ዝጋ ደጅዋን›› እያለ የሚዘፍን ማህበረሰብ፣

ህግና ስርዓት

‹‹ያዝ እጅዋን፣ ዝጋ ደጅዋን›› እያለ የሚዘፍን ማህበረሰብ …

‹‹ያዝ እጅዋን፣ ዝጋ ደጅዋን›› እያለ የሚዘፍን ማህበረሰብ፣ ‹አስገድዶ ክብረንጽህና የገሰሰ አምስት አመት ታሰረን ሲሰማ ይጎመዥ እንደሁ እንጂ አይማርም፡፡  | (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
.
አዲስ አበባ ከኮቪድ -19 ወረርሽን ጋር ተያይዞ 101 ልጆች ተደፈሩ፤ ወንድ ልጆችም አሉበት፡፡ የተደፈሩት ደግሞ በቤተሰቦቻቸው፣ በቤተ ዘመዶቻቸው፣ በጎረቤቶቻቸው፣ . . . . በአባቶቻቸውም ጭምር ነው፡፡ ይህ ማህበረሰባዊ ዝቅጠት የወለደው ሰይጣናዊ ጥቃት ነው፡፡ አንዳንዶች እንሰሳዊ/ ደመነፍሳዊ ይሉታል፤ እንስሳዊ ደመነፍስም ይህን አይፈቅድም፡፡

ከዚህ በላይ ማህበረሰብን የሚያፈርስ አደጋ የለም፡፡ . . . ልጆች በጠባቂዎቻቸው፣ መከታዎቻችን ባሏቸው ሰዎች ሲደፈሩ ከማየት የበለጠ የሚሰቀጥጥ ሰይጣናዊ ተግባር የለም፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ በዚህን ያህል ቁጥር ሲፈጸም፣ ያውም እነዚህ ሀኪም ቤት በመሄዳቸው አደባባይ የወጡ ናቸው፡፡ በየቤቱ ተደብቀው የቀሩት ከዚህ እንደማይተናነሱ እገምታለሁ፡፡

ከዚህም በላይ በአዲስ አበባ ከ14 -17 አመት ያሉ ልጆች እራሳቸውን እያጠፉ እንደሆነ እየተነገረ ነው፤ የእነዚህ ልጆች ራስን ማጥፋት ምክንያትስ ምንድነው? እንዲህ ያለው አስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸው እንደሆነስ?

ለካ ህጻናትን አስገድዶ መድፈር ያልበዛው፣ ማህበረሰቡ ህጻናቱን ስለሚንከባከብ አልነበረም፤ ኑሮ ባተሌ አድርጎት፣ ጊዜ ባለማግኘቱ ነው፡፡ ይኸው ጊዜ ሲያገኝ የገዛ ልጁን፣ የገዛ ቤተሰቡን፣ ቤተዘመዱንና ጎረቤቱን ይደፍር ገባ፡፡ ሙሉ በሙሉ ከተሞች በተዘጉባቸው አውሮፓና አሜሪካ እንዲህ አይነቱ ወንጀል አልተፈጸመም፤ ሊታሰብም አይችልም፤ በርግጥ ቀድሞም ቢሆን፣ የአስተሳሰብ መናወጥ ያለባቸው ናቸው በምእራቡ አለም ይህን አይነቱን ተግባር የሚፈጽሙት፡፡ እናም እድሜያቸውን ሙሉ ከማህበረሰቡ ተገልለው በወህኒ ይኖራሉ፡፡

በሀገራችን በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ የሚሰጠው ቅጣት በተደፋሪዎች ላይ የሚሳለቅ ነው፤ በሬና ፈረስ የሰረቀ፣ ህጻን ከደፈረ ሰው በበለጠ እስራት የሚቀጣበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ወዳጄ አበረ አያሌው እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ አጋርቶት እንዳነበብኩት፣ በቡሬ ከተማ አስገድዶ ደፍሮ የልጅቱን ክብረ ንጽህና ገስሶ፣ አምስት አመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ የሚያስቀው ደግሞ፣ ሰብሳቢው ዳኛ አቶ አበራ ገበየሁ፣ ‹‹ሌሎችንም ለማስተማርና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ›› ፍርዱን እንደሰጡ ማስታወቃቸው ነው፡፡ . . . ‹‹ከእሷ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት›› እያለ የሚዘፍን ማህበረሰብ፣ አስገድዶ ክብረንጽህና የገሰሰ አምስት አመት ታሰረን ሲሰማ ይጎመዥ እንደሁ እንጂ አይማርም፡፡

ምን መደረግ አለበት?

እነዚህን አውሬዎች ለህዝብ በየቴሌቪዥኑ ማሳየት፣ ማንነታቸውን ማጋለጥ፣ ማህበረሰቡ እራሱን ከነዚህ ሰዎች እንዲጠብቅ ማድረግ፣ የመጀመሪያው ተግባር መሆን አለበት፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች አንድ ጊዜ ብቻ ጥቃቱን አድርሰው እንደማይቀመጡ፣ በተደጋጋሚ እንደሚፈጽሙት በርካታ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ ከአስር አመት በላይ ታስረው ሲወጡ እዚያው ወንጀል ላይ የተያዙ በርካቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው እንዲህ አይነት በሽተኛ ሰዎች እድሜያቸውን ከማህበረሰብ ተገልለው በማረሚያ ቤት የሚያሳልፉት፡፡ በሀገራችንም ይህ መደረግ አለበት፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top