Connect with us

ክቡርነትዎ!… አልገባኝም?!

ክቡርነትዎ!... አልገባኝም?!

ፓለቲካ

ክቡርነትዎ!… አልገባኝም?!

ክቡርነትዎ!… አልገባኝም?!
(እሱባለው ካሣ)

በበጎ አሳቢነታቸው የማከብራቸው የአገሬ ጠ/ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ ወይንም የችግኝ ተከላ የፊታችን አርብ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀምር በሶሻል ሚድያ ገፃቸው ያሰፈሩት ማስታወሻ በግሌ ትልቅ ብዥታን ፈጥሮብኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ማስታወሻቸው ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምን ቢሆንም፤ አምስት ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን ብለዋል።

አያይዘውም እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን እንደ ጠበቀ አሻራውን ማሳረፍ የሚችልበትን መንገድ ይመቻቻል ማለታቸውን አንብበናል።

እስቲ አስቡት?!… አምስት ቢልየን ችግኞችን ለመትከል ምን ያህል ሕዝብ ሊንቀሳቀስ ይችላል? ዕቅዱን መነሻ አድርገን አንድ ሰው በነፍስ ወከፍ አምስት ችግኞችን ቢተክል ብለን ብናሰላ ወደ አንድ ቢልየን የሰው ሀይል ያስፈልገናል። ይኸ ሀይል ከቻይና ወይንም ከህንድ ኢምፖርት እናደርጋለን ካልተባለ በስተቀር የለንም። ለጊዜው የጠቅላላ ህዝባችን ቁጥር 100 ሚልየን መነሻ ብናደርግና ግማሹ ወጣት ሀይል ነው የሚለውን ብንይዝ ቢያንስ 20 እና 30 ሚልየን ወጣት በችግኝ ተከላው ላይ ማሳተፍ እንችል ይሆናል። ግን እንዴት? የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አስግቶን አገር አቀፍ ምርጫ ለማሸጋገር ህገመንግስት እስከማሻሻል ተጉዘናል።

አንዳንድ ተቀናቃኞች ወረርሽኙ ባለበት ሁኔታም ቢሆን ምርጫ ማካሄድ ይቻላል በሚል እየሞገቱም ጭምር ለህዝብ ጤና ጥበቃ ሲባል ምርጫው ተሸጋግሮአል ብለናል።

በሌላ በኩል ለምርጫ ይወጣልተብሎ ከሚገመት ህዝብ ቁጥር ያልተናነሰ የሚሳተፍበት የችግኝ ተከላ እንዲካሄድ ጥሪ እያቀረብን ነው።

እንዴት ነው ነገሩ? ምርጫ ሲሆን አይቻልም፣ ችግኝ ተከላ ሲሆን ይቻላል ማለት ነው? ሌላው ቀርቶ አገሪቱ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር መሆንዋ፣ ህዝባዊ መሰባሰብ መከልከሉ እንደምን ተዘነጋ?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ርቀትን በመጠበቅ፣ በመጠንቀቅ ችግኝ መትከል ከተቻለ፤ በተመሳሳይ መንገድ ምርጫ ማካሄድ ያልተቻለው ወይንም የማይቻለው ለምንድነው?

ክቡርነትዎ፤ በአጭሩ እየሆነ ያለው ነገር አልገባኝም። ከምር ለህዝብ ጤና ጥበቃ ቅድሚያ የሚሰጥ ከሆነ እንደምርጫው የችግኝ ተከላውም ቢቆየንስ?

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top