Connect with us

አምንስቲ ሁሌም ከተቃዋሚዎች ወገን ነው

አምንስቲ ሁሌም ከተቃዋሚዎች ወገን ነው

ህግና ስርዓት

አምንስቲ ሁሌም ከተቃዋሚዎች ወገን ነው

አምንስቲ ሁሌም ከተቃዋሚዎች ወገን ነው፡፡ የዛሬውን ከተጠራጠርነው የትናንቱም ግማሹ ውሸት ነው ማለት ነው፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

የአምንስቲ ሪፖርት የመነታረኪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ እኔን ያሰጋኝ ደግሞ ሌላ መንግስት ሲመጣ በዚህኛው ላይ ምን መሳይ ዶክመንተሪ ሊሰራ ይሆን የሚለው ነው፡፡ አምንስቲ ሲያደርግ ከቆየውና አሁን ከሚያደርገው ተነስተን ስንገምተው ለተቃዋሚዎች የሚራራ አንጀት፣ ለመንግስት ተገዳዳሪዎች በፍቅር የሚወድቅ ልብ እንዳለው ነው፡፡

አማራና ኦሮሚያ ሪፖርቱን አጣጥለውታል፡፡ አምንስቲ ያለው እግዜር ካለው እኩል ይቆጠራል ሲሉ የነገሩን ሰዎችም ዛሬ አምንስቲ ወገንተኛ እንደሆነ ሊያሳምኑን ሞክረዋል፡፡ አንዳንድ ሚዛናዊ ሰዎች አምንስቲ የኮነነው የመንግስት ሰብአዊ መብት ጥሰት ውሸት ነው አላሉም፤ ይልቁንም ያላካተተው የሌላው ጎራ የሰብአዊ መብት ጥሰትስ ነው ጥያቄያቸው፡፡

ከተግባሩ የገባን አምንስቲ ስልጣን የያዘውን ይኮንናል እንጂ ስልጣን የሚሻውን አያጨናግፉም፡፡ በዚህ ስሌት ተከበብኩ ያለው ሰው አደረሰ የተባለው ቀውስ ሪፖርቱ ይዘለዋል፤ መንግስት አደረሰው የተባለውን ደግሞ አድምቆ ይጽፈዋል፡፡

ዛሬ የአምንስቲን ሪፖርት ልክ ነው የሚሉ ወገኖች ትናንት የሊበራሎች ፈረስ የምዕራባውያን ቅጥረኛ ነው ሲሉን የነበሩ ናቸው፡፡ ትናንት ገበያችን ክፍት ስላልሆነ፣ ኢኮኖሚውን ስላልጨፈሩበት በሰብአዊ መብት ጥሰት ስም የውጪ ሃይሎች ሊጠመዝዙን የሚመጡበት መንገድ አምንስቲ ነው ብለውን ነበር፡፡ ዛሬ አምንስቲ አፍረጠረጠው እያሉ ነው፡፡

ያኔ አምንስቲ በተነፈሰ ቁጥር ይሄ ሰው በላ መንግስት እየተባለ ከሪፖርቱ ቁጥር ጋር ሐጢአቱን ይቆጥሩ የነበሩ ደግሞ ተገልብጠዋል፡፡ አምንስቲ ወገንተኛ እንደሆነ እየነገሩን ነው፡፡ እንደዚያ ከሆነ አምንስቲ በኢህአዴግ መራሹ መንግስት ላይም ያወጣቸው የነበሩ ክሶች ግማሾቹ ሀሰት ናቸው ማለት ነው፡፡

ከአምንስቲ ምን እንማራለን? ራስን ማየት፤ ሪፖርቱን የዓለም መጨረሻም አለማድረግ፡፡ ዛሬ አለ የተባለው የመብት ጥሰት ምን ድረስ ነው የሚለውን ራስን መፈተሽ፡፡ ብልጽግና የመላዕክት የጸጥታ ሰዎች አላሰማራም፡፡ አንድ ሀገርና አንድ መሬት እየኖርን ነው፡፡ ግለሰብ የሚያሳድዱ የጸጥታ ሃይሎች እድሉን ቢያገኙ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ማሰብ ነው፡፡ ኢህአዴግን የበተነው አምንስቲ አይደለም፡፡ ተቃዋሚውን ለመንግስት አፈ ቀላጤነት ያበቃውም አምንስቲ አይደለም፡፡ አምንስቲ ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ቀን ጠበቆ እርምጃ ለሚወስደው ህዝብ መጠንቀቁ ከሁሉ የሚበልጥ ነው፡፡

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top