Connect with us

የዴሪክ ቻቬን ባለቤት ፍቺ ጠየቀች

የዴሪክ ቻቬን ባለቤት ፍቺ ጠየቀች
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የዴሪክ ቻቬን ባለቤት ፍቺ ጠየቀች

ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን በጠራራ ፀሀይ ህዝብ እያየው አንገቱ ላይ ረግጦት ህይወቱን ያሳለፈው የሚኒያፖሊስ የፖሊስ ባልደረባ ዴሬክ ቻውቪን አርብ ዕለት ወደ እስር ቤት ወርዱዋል።

ይህንን ተከትሎም ላለፉት 10 ዓመታት የትዳር አጋሩ ሆና የቆየችውና የቀድሞዋ የሚኒሶታ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ባለቤቱ ኬሊ ቻውቪን በጠበቃዋ አማካኝነት የፍቺ ጥያቄ ለፍርድ ቤት አስገብታለች።

በተፈጠረው ሁኔታ ልቤ ተሰብሩዋል ለፍሎይድ ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ ብላለች።

አለምን በእጅጉ ያስደነገጠው ዘግናኝ ድርጊትን በዋንኛነት የፈጸመው የቀድሞው የፖሊስ አባል ዴሪክ ቻቬን በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን እና በሶስተኛ ደረጃ የሰው መግደል ወንጀል እንደሚከሰስ የፍርድ ሂደቱም ከዘጠኝ ወራት እስከ ሁለት አመታት ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል።

ክስተቱ ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን በመላው አሜሪካ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስከትሏል፤ የፖለቲከኞችም ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

ባለፈው ስኞ ዴሪክ ቻቬን መሳሪያ ያልያዘዉን የ46 ዓመቱን ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድን አንገቱ ላይ በመንበርከክ አንቆ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉ ይታወቃል።

“መተንፈስ አልቻልኩም”የሚለው የጆርጅ የመጨረሻ ድምጽ ለበርካታ አሜሪካኖች የቁጣ እና የተቃውሞ አርማ ሆኗል።
Source: ABC News

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top