Connect with us

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በልጆችላይ የሚያስከትላቸው ተጽዕኖዎች

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በልጆችላይ የሚያስከትላቸው ተጽዕኖዎች ምንድን ናቸው ?

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በልጆችላይ የሚያስከትላቸው ተጽዕኖዎች

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በልጆችላይ የሚያስከትላቸው ተጽዕኖዎች ምንድን ናቸው?
ባለፈው የቀጠለ
(ሙሉጌታ ዜና የስነ – ባህሪ ባለሙያ በድሬቲዩብ)

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በልጆች ላይ የሚየስከትላቸውን ተጽዕኖዎችን ለመረዳት ያመቸን ዘንድ አልበርት ባነዱራ የሚባል የስነ-ልቦና ምሁር የነዳፈውን ጽንሰ ሃሳብ (Theory ) ማየቱ ተገቢ ይሆናል፡፡

አልበርት ባንዱራ የማህበራዊ ትምህርት ጽንሰ ሃሰብ (Social learning theory) ጠንሳሽ ሲሆን ያፈለቀው ጽንሰ ሃሳብ(Theory) ልጆች የሚማሩት ከሚያዩት ነገር ነው የሚል ድምዳሜ ላይ አድርሶታል፡፡ እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሰው እ.ኤ በ1960 ያደረገው የሙካራ ጥናት(experiment ) ነው፡፡

ይህ የሙከራ ጥናት ሰው መሳይ አሻንጉሊት ሙከራ ጥናት (Bobo Doll Experiment)ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን እድሜያቸው ከ3-6 አመት የሚደርሱ 72 ህጻናት የሙካራ ጥናቱ ላይ ኢዲሳተፉ አድርጓል፡፡

በዚህ ጥናት ላይ ያገኘው ግኝት ልጆች የሚመሩት በማየት እና አርዓያ ይሆናል በሚሉት ሰዎች ድርጊት ነው በእንግሊዘኛው Observational learning and modeling ይባላል፡፡ በእኛም ሀገር ነገር በአይን ይገባል ይባል የለ፡፡

ባንዱራ ይህንን መሰራታዊ ጥናት ካጠና ቦሃላ በዚህ ጽንሰ ሃሳብ( Theory) ላይ በመመስራት እና ሌሎች ጽንሰ ሃሳቦችን በማፍለቅ ቴሌቪዥን በልጆች ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖዎችን በጥናቶቻቸው አስቀምጠዋል፡፡

እነዚህም:
1.የባህሪ ቸግር/ቁጡ ፤ተናዳጅ ፤ግልፍተኛ ፤ተደባዳቢ መሆን (Aggression)
2.ፍርሃት (fear)
3.ድብርት (Depression)
4.ትኩረት ማጣት/Lack of concentration)
5.ርህራሄን ማጣት /Lack of empathy)

6.የጀርባ ህመም (Back pain)
7.ለልብ እና ስኳር በሸታ መጋለጥ(Cardiovascular & Diabetic disease)
8.የማህባራዊ ክህሎት ማነስ(Lack of social skill)
9 .ችግር የመፍተት ክህሎት ማነስ (Lack of problem solving skill)
10.የአይን ህመም/የአይን ድርቀት( Eye dryness )
11.የፈጠራ ክህሎት ማነስ(Lack of creativity)
12.የእንቅልፍ መዛባት እና ቅዥት (Sleep disturbance and nightmare))

13. የቴሌቪዥነ ሱሰኛ( Addictive ) መሆን እና ሌችም አሉታዊ ተጽህኖዎች ያሉት መሆኑን ጥናቶቹ አረጋግጠዋል፡፡

የእያንዳንዱን ችግር ዝርዝር እና ሌሎች ተጽህኖዎችን ችግር ለማወቅ እና በልጆች ስነ-ባህሪ ላይ በሚታላለፈው ትምህርርት አዘል የቴሌግራም ቻናላችንን (የልጆች ሥነ-ልቦና /Child Psychology) http://t.me/tnx6778 ) በመቀላቀል መረዳት ይቻላል፡፡

በቀጣይ መፍትሄዎቹ ላይ ሃሳቦችን እናቀርባለን …. እስከዚያው ቸር እንሰንብት

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top