Connect with us

ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም

ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም
Photo Facebook

ባህልና ታሪክ

ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም

ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም

የሕወሓት ሊቀመንበር መለስ ዜናዊ እና የደኅንነቱ ሹም ክንፈ ገብረ መድኅን ወደ ግዮን ሆቴል ሲገቡ ይታያሉ።

የሚሊተሪ ዩኒፎርም ለብሶ የሚታየው የቀድሞው ጦር (ደርግ) መኮንን የነበረው ኮሎኔል አስራት ነው። ኮሎኔል አስራት በሕወሓት ከተማረከ በኋላ ከኢህአዴግ ጋር ተሰልፎ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ሀላፊነት ደረጃ ድረስ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላም የግርማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አስከሬን ከተቀበረበት የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጽ/ቤት ለማውጣት የተዋቀረውን ግብረ ኃይል ያስተባበረ ነው።

አብዮት ልጇን ትበላለችና ኮሎኔል አስራት የቀይ ሽብር ተዋናይ ነበር ተብሎ ወደ ወህኒ ቤት የወረደ ሲሆን፤ በወህኒ ቤትም እያለ “በህመም” ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ መሆኑ ታውቋል።

የደኀንነት ሹም የነበረውም ክንፈ በሌላው የሕወሓት ታጋይ ሻለቃ ፀጋዬ በጥይት ተደብድቦ ተገሏል። የሕወሓት መሪ የነበረው ለገሰ ዜናዊ በኋላ መለስ ዜናዊም አመራርነቱን እንደጨበጠ በ 57 አመቱ በሞት ተለይቷል።

ግንቦት 20 ዛሬ 29ኛ አመቱ ሲታሰብ በፎቶው ላይ የምናያቸው ሶስቱም አመራሮች በሕይወት የሉም። ግንቦት 20ም ከብሔራዊ በዓልነት ተሽሯል። የግንቦት 20 ፊት አውራሪዎችም ከፊሎቹ በሞት ሲለዩ፣ ከፊሎቹ አራት ኪሎን ተሰናብተው መቐለ መሽገው ቀሪ ጊዜያቸውን እያሳለፉ ነው ።

ቦ ጊዜ ለኩሉ! #phetros_ashenafi

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top