Connect with us

ጠቅላዬ ጣናን እንደምን ዘነጉት?

ጠቅላዬ ጣናን እንደምን ዘነጉት?
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ጠቅላዬ ጣናን እንደምን ዘነጉት?

ጠቅላዬ ጣናን እንደምን ዘነጉት?
(ጫሊ በላይነህ በድሬቲዩብ )

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በፌስቡክ ገፃቸው ተከታይዋን አጭር ሐተታ ዛሬ አስፍረው ተመለከትኩኝ። እንዲህ ይላል። “ብሔራዊ የተፈጥሮ ስጦታዎቻችንን ለዘላቂ ልማት ማዋል የሀገራዊ ብልጽግና መስፈንጠሪያ ቁልፍ ነው። ….”ይላል።

ጠቅላዬ ስለየትኛው ሐብት እያወሩ እንደሆነ አልገባኝም። አያይዘው የለጠፏቸውን ምስሎች በማየት ምናልባት ስለአዲስአበባ የወንዞች ልማት እየነገሩን ሊሆን እንደሚችል ገምቻለሁ። ንግግሩ ስለየትኛውም ሐብት ይሁን መሰረተ ሀሳቡ ላይ ምንም አይነት ልዩነት የለኝም። የተፈጥሮ ሐብቶቻችን ለልማት የማዋል ጉዳይ ብዙ የሚያከራክር አይደለም።

እዚህ ጠቅላዬ ፖስት ስር ከተሰጡ አስተያየቶች ብዙዎች እንደጣና ያሉ በእምቦጭ አረም የተወረሩ ሐብቶች ችላ መባል ቅሬታቸውን ገልፀዋል።እኔም ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል ነኝ።

ጠቅላዬ በዚህ ሰአት በክረምቱ ወራት ለመትከል ከሚያስቡት አምስት ሚልየን ችግኝ በላይ በመጥፋት አፋፍ ላይ የሚገኘው እና መሰል በአረም የተወረሩ የተፈጥሮ ሐብቶች ያሉበት ሁኔታ ያሳስበኛል። እነዚህን ፈጥኖ መታደግ መልካም ስም ያስገኛል። አሻራው ለትውልድም ይተርፋል።በተቃራኒው አለመታደግ ለትውልድ የሚተርፍ ክፉ ስምን አትሞ ማለፍ ይሆናል።

ጠቅላዬ ጣናን ችላ ብለው ስለአዲስአበባ ወንዝ ልማት ጭንቅ ጥብብ ቢሉ፣ ጣናን ዘንግተው ስለችግኝ ተከላ ጠቀሜታ ነጋ ጠባ ዲስኩር ቢያሰሙ ሁኔታውን ለተረዳ ሁሉ እንደፌዝ የሚታይ እንጅ ከቁምነገር የሚጥፈው ሊኖር አይችልም። ምክንያቱም የአካባቢ ጥበቃ ወይንም ልማት ጉዳይ ያለውን እየጠበቁ እንጂ ሲጠፋ ቁጭ ብሎ እየተመለከቱ እንዲሆን አይፈቅድምና ነው።

ጠቅላዬን በድፍረት የምተቸው ጉዳዩ የአማራ ክልል መንግስትን በቀጥታ የሚመለከተው መሆኑን ዘንግቼ አይደለም። ቢያንስ ህዝብ ያዋጣው ገንዘብ ለምን ስራ ላይ ሳይውል እንደቀረ የመጠየቅና ከዚህ ቀደምም ጣናን አስመልክቶ ለህዝብ የገቡትን ቃል መጠበቅ ይገባል በሚል የቀረበ ነው።በዚህ ላይ ደግሞ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና እንክብካቤ በክልል ብቻ የሚታጠር አለመሆኑ የአዲስአበባ ልማቶች ተሞክሮ ይናገራልና ነው።

የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ውጤታማነቱ አንዱና ትልቁ በእጅ ያለውን መንከባከብና መጠበቅ መሆኑን ለክቡርነትዎ ሳስታውስ ንግግሬን በድፍረት እንደማይወስዱብኝ በመተማመን ነው።

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top