Connect with us

ዛሬም የአዲስ አበባ ቅርሶች ከመፍረስ አደጋ አልዳኑም

ዛሬም የአዲስ አበባ ቅርሶች ከመፍረስ አደጋ አልዳኑም

ባህልና ታሪክ

ዛሬም የአዲስ አበባ ቅርሶች ከመፍረስ አደጋ አልዳኑም

ዛሬም የአዲስ አበባ ቅርሶች ከመፍረስ አደጋ አልዳኑም፤
የዳግማዊ ምኒልክ የግራ ወንበር ዳኛ የተክለማርያማ ባሻ ቤት አደጋ ተጋርጦበታል፡፡ ከተማዋ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርስ የማልማት ሀሳብ በተቃራኒው እየሄደች ነው፡፡
******
በቅርቡ የሴጣን ቤት ጉዳይ ብዙ አወያይቶ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ቅርሶች ከስጋት የሚያድናቸው አካል አልተገኘም፡፡ አዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍልስፍና በተቃራኒው ቆማለች፡፡ እድሜ ጠገብ ቤቶቿ በምስጢር እንዲፈርሱ ስራ እየተሰራ ነው፡፡


ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ትናንት በአዲስ አበባ የሚገኘው እና የዳግማዊ ምኒልክ የግራ ወንበር ዳኛ የተክለማርያም ባሻ መኖሪያ የነበረው 112 ዓመት ያስቆጠረ ቅርስ እንዲፈርስ ተወስኖበታል፡፡ በቤቱ እየተገለገሉ ያሉ ሰዎችም ማስፈራሪያ ደርሶባቸው በሦስት ቀን ውስጥ እቃቸውን ይዘው የገቡበት እንዲገቡ የተነገራቸው መሆኑም የድሬቲዮብ ምንጮች ሰምተዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነባር የሀገር መገለጫ የሆኑ ቅርሶች ይበልጥ እንዲለሙ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚቃረነው ቅርሶችን በምስጢር የማፍረስ ዘመቻ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ይህ ደግሞ ቅርስ ነው ብሎ የመዘገበው አካልና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አንዳችም እውቅና ሳይኖረው የሚደረግ ሲሆን በቅርስነት የተመዘገበው ይህ ቤት እንዲፈርስ የተወሰነበት ምክንያት ግን ቅርሱን ለያዙት አካላት በደብዳቤ አልተገለጸም፡፡
ሴጣን ቤት በሚል የሚታወቀው የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት በደብዳቤ እንዲፈርስ ከተወሰነ በኋላ በተፈጠረው ቅሬታ ሊተርፍ ችሏል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top