Connect with us

ብልጽግና የትግራይ ወጣቶችን ትግል እያከሸፈ ነው

ብልጽግና የትግራይ ወጣቶችን ትግል እያከሸፈ ነው
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ብልጽግና የትግራይ ወጣቶችን ትግል እያከሸፈ ነው

ብልጽግና የትግራይ ወጣቶችን ትግል እያከሸፈ ነው፡፡ ወጣቶቹ ህወሃትን እንደ ተቀየሙ ገለጹ እንጂ በብልጽግና ፍቅር ኣላበዱም፡፡ | ከሰለሞን ሓይለ

በትግራይ የተለያዩ ኣካባቢዎች ሰሞኑን በህወሃት ስም የሚነግዱ ቡድኖችን የመቃወም እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ እንቅስቃሴው መነሻውም መድረሻውም ህወሃትን ጥላቻ አይደለም፡፡ በህወሃት ስም የነገዱ፣ የከበሩ፣ ኣንጋፋ ታጋዮችን ሲያሳድዱ የኖሩ ጡረተኞችን በቃኝ ለማለት ነው፡፡

በዚህ ኣስታኮ የወረዳ ኣስተዳደር ጥያቄዎች፣ በፖሊስ የተገደሉ ንጹሃን ጉዳይ፣ ህዝቡን ለፖለቲካ መጠቀሚያ የማድረግ ኣባዜን በቃ የማለት የፈንቅል እንቅስቃሴ ተቀጣጥሏል፡፡ እንቅስቃሴው በስሙ ለተነገደበትና ምንም ጥቅም ላላገኘው የትግራይ ህዝብ እፎይታን ለማምጣት ነው እንጂ ሌላ ኣላማ የለውም፡፡

ብልጽግና ግን የትግራይ ወጣቶችን ትግል እያከሸፈ ነው፡፡ ምናልባት ብልጽግና ከህወሃት ጋር በድብቅ ሽርክም ይሆናል፡፡ ትግሉን ሌላ መልክ ለመስጠትና መራሁት ለማለት የሚያደርገው ሩጫ የከፋ ጅብ ሊበላን ነው ብለው ወጣቶቹ እንዲሸሹ ያደርጋል፡፡

ውሸት የሚጠላው የትግራይ ህዝብ በመንደሩ ያልተፈጸመ ዱላ ይዞ ሰልፍ ፎቶ ከወለጋና ከሀረርጌ እየተዋሱ መለጠፉ ኣላማው ምንድን ነው? የትግራይ ወጣት ከህወሃት መቀያየሙ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የታጋይ ስየ ኣብረሃ ቃለ መጠይቅ ይቀርባል ብሎ ትግራይ ቴሌቨዥን በሰጠው መግለጫ ላይ ወጣቱ የመለሰውን ኣስተያየትና ኮሜንት ማየቱ ብቻውን ይበቃል፡፡ ጡረተኞች ኣርፈው መጦር ኣልፈለጉም፡፡ የታጋይ ስየ ምክር ጦርነት ለማንም ኣይበጅም የሚለውን መስማት ኣልፈለጉም፡፡ የፈለጉት መጣልህ ሊበላህ ነው እያሉ እድሜ ማራዘም ነው፡፡ ልጆቻቸው የት ናቸው? ቤታቸውስ? ንብረታቸውስ?

እውነቱ ይህ ነው፡፡ ብልጽግና ግን እሱን ኣፍቅሮ ኣመጽ ያነሳ የትግራይ ወጣት ያለ ይመስል ፕሮፖጋንዳውን ኣጧጡፎታል፡፡ የትግራይ ወጣት ከህወሃት መሪዎች ቢቀያየምም ከብልጽግና የሚታረቅበት ምክንያት ኣልተፈጠረም፡፡ ብልጽግና ዛሬም በሀሰት ወሬ የማያውቀውን ጥያቄና ትግል የመራው ለመምሰል መሞከሩ ከትግራይ ወጣቶች ልብ በጣም መራቅ እንደሚፈልግ ያሳያል፡፡

የትግራይ ወጣት ለራሱ ራሱ ያውቃል፡፡ ትግሉን ለመቀልበስ እኛ መራነው የሚለው ግን የሚያስተዛዝብ ነው፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top