Connect with us

የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲነሳ ተጠየቀ

በአዲስ አበባ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲነሳ ተጠየቀ
Photo: Ethiopian Reporter

ህግና ስርዓት

የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲነሳ ተጠየቀ

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ በኮድ ሁለት የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ፣ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር በመፍጠሩ እንዲነሳ ተጠየቀ።

ጥያቄውን ያቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም ለመከታተል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት የተቋቋመው መርማሪ ቦርድ ነው። መርማሪ ቦርዱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት የተሰጠውን የሚኒስትሮች ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ባለፈው ሳምንት በገመገመበት ወቅት፣ በግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብን በመሠረታዊነት የሚስማማበት ቢሆንም የተገፈለገውን ውጤት እንዳላስገኘ አመልክቷል።

የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሰንበት በግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ የመንግሥት ሠራተኞች ከቤታቸው እንዲሠሩ፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችም እንዲዘጉ መደረጉን ታሳቢ ያደረገ ቢሆንም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተፈለገው በቤታቸው መቀመጥ አለመቻላቸውን ገልጸዋል።

በግል ተሽከርካሪዎች ላይ ከተጣለው ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ በተጨማሪ የሕዝብ ትራንስፖርቶችም በግማሽ የማጓጓዝ አቅማቸው አገልግሎት እንዲሰጡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተወሰነ በመሆኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎችን ከቤት ውጪ እንቅስቃሴ መግታት ባላመቻሉ የተፈጠረው ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ለቫይረሱ ሥርጭት ምቹ እንደሆነ ገልጸዋል።

በከተማዋ 220,000 የግል ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ከከተማ አስተዳደሩ እንደተረዱ የተናገሩት የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ፣ የነዋሪዎች እንቅስቃሴን እንደተፈለገው መግታት ባለመቻሉ በግል ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ገደብ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎት ጫና መፍጠሩን አስረድተዋል።

በመሆኑም የሚኒስትሮች ኮሚቴ በተጣለው ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ የሚችልበትን መንገድ እንዲያስብ ጥያቄ አቅርበዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የሚኒስትሮች ኮሚቴ አባል የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ ችግሩን እንደሚረዱት በመግለጽ በሚኒስትሮች ኮሚቴ እንደሚታይ ገልጸዋል።(ሪፖርተር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top