Connect with us

ህወሓት ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤት እንኳን እንዳይሰራ የሚከለክል …

"ህወሓት ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤት እንኳን እንዳይሰራ የሚከለክል የሃላ-ቀርነትና የድንቁርና ጠበቃ ሆኗል!! " (ነብዩ ስሑል ሚካኤል ~ ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ )
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ህወሓት ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤት እንኳን እንዳይሰራ የሚከለክል …

“ህወሓት ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤት እንኳን እንዳይሰራ የሚከለክል የሃላ-ቀርነትና የድንቁርና ጠበቃ ሆኗል!! ”
(ነብዩ ስሑል ሚካኤል ~ ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ )

የሽረ ህዝብ ከሚያነሳቸው አያሌ ጥያቄዎች መካካል ክብርት ቀዳማይት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በሽረ ከተማ ጥራቱ የጠበቀ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰራ ያበረከቱት 20 ሚልዮን ብር በህወሓት ካድሬዎች ተበልቶ የጠፋበት የመንግስታዊ-ሌብነት ተግባር አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

እንደሚታወቀው የዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ ክብርት ቀዳማይት እመቤትዋ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ተመሳሳይ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሰሩ ሲሆን በትግራይ ክልል በሽረ ከተማ እንዲሰራ ሙሉ ባጀቱ ትግራይን እያስተዳደረ ላለው መንግስት ገቢ ተደርጎ ነበር፡፡

የሽረው ትምሀርት ቤት ግን እስካሁን ክብርት ቀዳማይት እመቤትዋ ካኖሩት የመሰረት ድንጋይ ሌላ ምንም ነገር ሳይሰራለትና ባጀቱም የት እንደገባ ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡

የትግራይ ህዝብ ልዩነቱን እያየ ነው፤ ማን በእኩልነት ዓይን አይቶት ልጆቹን የሚማሩበት ትምህርት ቤት ሊሰራለት ይተጋል፤ ማን የተማረ ትግራዋይ እንዳፈጠር የሌባ-ሻይ ስርዓት አይነት የቁርኝት ሰንሰለት እየዘረጋ ይውላል ህዝብ እያየው ነው፡፡

ለማንኛውም ክብርት ቀዳማይት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽን ስለ በጎ ሃሳብዎና ተግባርዎ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን!!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top