Connect with us

ጌታቸው አሰፋ ዛሬም ያልተቋጭው ድራማ ርዕስ

ጌታቸው አሰፋ ዛሬም ያልተቋጭው ድራማ ርዕስ

ፓለቲካ

ጌታቸው አሰፋ ዛሬም ያልተቋጭው ድራማ ርዕስ

ጌታቸው አሰፋ ዛሬም ያልተቋጭው ድራማ ርዕስ፤ | ከስናፍቅሽ አዲስ

ረዥም ድራማ ምን ቢያምር አሰልቺና ደስ የማይል ነው፡፡ የማይችል ተዋናይ ደግሞ ሁሌም ከመድረኩ አልወርድ ካለ ችግሩ ብሶ ቀፋፊ ብቻም ሳይሆን አሰልቺም ይሆናል፡፡

ጌታቸው አሰፋ አንድ ሚሊዮን ጊዜ የሰበር ዜና ርዕስ ሆኗል፡፡ ሰበር ዜናው ከገለጡት ሹሞች መካከል ክስ መሰረትንበት ያሉት አቃቤ ህግ የቀድሞ ወዳጃቸውን ፍጻሜ ሳይመለከቱ አምባሳደር ሆነው ቢሯቸውን ለቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በግል ከጌታቸው አሰፋ ጋር ጠብ የለውም፡፡ ብዙ ሰበር ዜና ሰባሪዎች ግን የግብጽ ያህል ጠላት አድርገው ነጋ ጠባ የሰበር ዜናቸው ርዕስ ሆኗል፡፡ እስከመቼ ማንም አያውቅም፡፡

የጌታቸው አሰፋ ጉዳይ ከነገሩ መክበድ ቀሎ ድራማ የሚመስል ጨዋታ ሆኗል፡፡ ድራማው ማቆሚያ መጣቱ ግን ረብ የለሽ ድራማ ሳያስመስለው አልቀረም፡፡ አንዳንዶች በሀገር ውስጥ ችግሮች መታየት ሲጀምሩ የተቋረጠው የጌታቸው አሰፋ ድራማ በሌላ ሲዝን ሊቀጥል መተዋወቅ ይጀምራል እያሉ መቧለት ጀምረዋል፡፡ ቧልቱ መሰረተ ቢስ ነው ለማለት ግን አይቻልም፡፡

ጌታቸው አሰፋ የአንድ አምባገነን ስርዓት አንድ ባልደረባ ነው፡፡ ብቻውን ሠራዊት አይደለም፤ ብቻውን ሚዲያ አልነበረም፡፡ ብቻውን ሀገር አልሰለለም፤ ብቻውን ቀበሌ ጉቦ አልለቀመም፤ እሱ አንድ ሰው ነው፡፡

የኦሮሚያ መሬት ሲቸረቸር፣ ኦነግ ብሎ ኦዲፒ ወንድሙን ሲገድል፤ ሙስሊሙ የኮሙኒኬሽን ሰው ሙስሊሙን ሲያሳድድ፣ ጋዜጠኛው ጋዜጠኛውን የሚያስጨንቅ ህግ ሲያወጣ በመንፈሱ እንደ አውሊያ አዘዘን ካልተባለ ጌታቸው አንድ ሰው ነው፡፡ ጌታቸውን ማረሚያ መክተት የሀገሪቱን ሁሉ ችግር እንደሚፈታ ተስፋን በህዝቡ ላይ መከመሩ ሳይሳካ የቀረው ሳይጀመር ነው፡፡

ኢትዮጵያን የጎዳት ትንናንት አይደለም ዛሬስ የእናት ጡት ነካሽ የለም እንዴ? ነገን ጥሩ ለማድረግ ከትናንት ከጀመረን ዛሬን ከማበላሸት በስተቀርስ ምን ጥቅም እናገኛለን? ነገ ጥሩ የሚሆነው ዛሬ ጀምረን ሀገር ስንሰራ፣ ዛሬ ጀምረን አንድ ስንሆን ነው፡፡

ጌታቸው አሰፋ ድጋሚ መች እንደሚያዝ አላውቅም፡፡ አንዱ ጀብራሬ መልሶ ሰበር ዜና ይልና ከስድስት አልያም ከዘጠኝ ወር በኋላ ዳግም ኤርፖርት መያዙን ይነግረናል፡፡ ከዚያስ ድራማው አሰልችቶም ይቀጥላል፤

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top