Connect with us

ግብጽ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ሒደት ላይ ድርድር ለመቀጠል ተስማማች

ግብጽ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ሒደት ላይ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ድርድር ለመቀጠል ተስማማች
A worker walks with a piece of wood on his shoulder at the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), near Guba in Ethiopia. AFP

ፓለቲካ

ግብጽ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ሒደት ላይ ድርድር ለመቀጠል ተስማማች

ግብጽ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ሒደት ላይ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ድርድር ለመቀጠል ተስማማች። የግብጽ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “ከፍትሃዊ፣ ሚዛናዊ እና አጠቃላይ ስምምነት ለመድረስ በመጪዎቹ ጊዜያት በሚደረጉ ድርድሮች እና ውይይቶች ለመሳተፍ ግብጽ ሁልጊዜም ዝግጁ ነች” ብሏል።

ግብጽ ይኸን ያለችው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በቪዲዮ ውይይት አድርገው «የቴክኒክ ውይይቶችን ለመቀጠል» መስማማታቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው።

Workers perform measurements at the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), near Guba in Ethiopia. AFP

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ አቻቸው ካደረጉት ውይይት በኋላ «የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ለሁሉም አካላት በሚስማማ መፍትሔ ላይ መክረናል። የተሳሳተ ግንዛቤ የነበረባቸውን ጉዳዮች አጥርተን ተነጋግረናል። በውኃ ሚኒስትሮቻችን አማካኝነት የቴክኒክ ውይይቶችን ለመቀጠል እና ያልተቋጩ ጉዳዮችን አጠናቅቀን ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለመቀየስ ተስማምተናል» ብለው ነበር።

Workers walk next to a power shovel at the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), near Guba in Ethiopia. AFP

ኢትዮጵያ እና ግብጽ በግድቡ ጉዳይ መስማማት ተስኗቸው ውዝግቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ደርሷል።

ግድቡን በውኃ መሙላት እና ሥራ ማስጀመር ኑሯቸው በናይል ወንዝ ላይ የሆነ 100 ሚሊዮን ዜጎችን አደጋ ላይ ይጥላል የሚል ደብዳቤ ግብጽ ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ደብዳቤ ጽፋለች። የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው «ኢትዮጵያ ግድቡን በውኃ ለመሙላት የግብጽን ፈቃድ እንድትጠይቅ በሕግ አትገደድም» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በአሜሪካ እና ዓለም ባንክ አማካኝነት በዋሽንግተን የጀመሩት ድርድር ስኬታማ አልሆነም። በድርድሩ አሜሪካ ያዘጋጀችውን ስምምነት ግብጽ ብትፈርምም ኢትዮጵያ ጭርሱን በመጨረሻው ስብሰባ ሳትገኝ ቀርታለች። dw amharic

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top