Connect with us

ጥቂት ምክር ~ ለትግራይ ብልፅግና ፓርቲ

ጥቂት ምክር ~ ለትግራይ ብልፅግና ፓርቲ

ፓለቲካ

ጥቂት ምክር ~ ለትግራይ ብልፅግና ፓርቲ

ጥቂት ምክር ~ ለትግራይ ብልፅግና ፓርቲ
(እሱባለው ካሳ)

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ነብዩ ስሑል ሚካኤል በህወሓቶች ግፍ ማዘኑን እንዲህ ሲል ይገልፃል።
“ተጋሩ በገዛ አገራቸውና በቤታቸው ደጃፍ ትግርኛ በሚናገሩ ግፈኞች በጥይት ግንባራቸው ተመተው በጭካኔ ሲገደሉና የተለያዩ ግፎች ሲደርስባቸው እንዳልሰማ የሚሆንና ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚሞክር “የትግራይ አክቲቪስትና ሚድያ” የማየት ያክል የሚያሳምም ነገር የለም” ይላል።

ያያይዝናም “ትግራይ የጥቂት ሰዎች የስርቆትና የግፍ ደሴት የሆነችበት የክህደት ምዕራፍ በአስቸኳይ ማብቃት አለበት፡፡ ትግራይ የእኩልነት፣ የተስፋና የብልፅግና አለም ማድረግ የመፃኢ እድላችንና የብሩህ ተስፋችን ብቸኛ ማረጋገጫ ዋስትናችን ነው” በማለት ያሳርጋል።

ነብዩ እንዲያው ድከም ሲለው ነው። ሲጀምር ህወሓት በተነካ ቁጥር ግር ብለው የውግዘት፣ የእርግማን ውርጅብኝ ሲያወርዱ የሚውሉ የፌስቡክ አርበኞች እንጂ አክቲቪስቶች አይደሉም። “ሀሳብ የነጠፈባቸው፣ ቀለብተኞች” የሚለው ጥሩ ይገልፃቸዋል። ለእነሱ የመንጋ መሪውን ተከትሎ መሳደብ ወይንም ማደናነቅ ደመወዝ የሚያስገኝላቸው መደበኛ ሥራ ነው።አንድ ሰራተኛ ደግሞ ሥራውን በፈቃዱ ለመተው ካልወሰነ በስተቀር አሰሪውን ሊገዳደር አይችልም።እነዚህን የግሪሳ ወፎች ከሆዳቸው ባለፈ የሚያሳስባቸው ነገር የለምና ስለአገርና ስለህዝብ ደህንነት ማውራት በከንቱ ጉንጭን ማልፋት ይሆናል። ቀድሞውኑ ህዝቡ በራሱ አውቋቸው፣ አንቅሮ እየተፋቸው ነውና።

እናም ህወሓት 27 ዓመታት በመሀል አገር የሰለጠነችበትን የግፍ አገዛዝ ቆርጦ መጣል የሚችለው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ህዝቡ ግፍ በቃኝ፣ ጭቆና በቃኝ፣ መሞት… መሰደድ በቃኝ፣ የነቀዘ አመራር በቃኝ፣ የቡድንተኝነት ሥልጣን በቃኝ፣ የበይ ተመልካች መሆን በቃኝ…ያለ ዕለት ሁሉም ነገር ያከትማል። እናም ነብዩ ሆይ፤ ብቸኛው ሰላማዊ መንገድ ህዝቡን ማንቃት፣ ማደራጀት፣ ለመብቱ፣ ለነፃነቱ እንዲታገል መደገፍ ብቻ ነው።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top