Connect with us

ፕሮፌሰር አንድርያስ እንኳን ለዚህ ለዚያ የሀሳብ ትውልድ የከበደ ጌጥ ነው

በሀሳቡ አለመስማማት ይቻላል፤ ፕሮፌሰር አንድርያስ እንኳን ለዚህ ለዚያ የሀሳብ ትውልድ የከበደ ጌጥ ነው

ፓለቲካ

ፕሮፌሰር አንድርያስ እንኳን ለዚህ ለዚያ የሀሳብ ትውልድ የከበደ ጌጥ ነው

በሀሳቡ አለመስማማት ይቻላል፤ ፕሮፌሰር አንድርያስ እንኳን ለዚህ ለዚያ የሀሳብ ትውልድ የከበደ ጌጥ ነው፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ

አንድርያስ ዓለም አቀፋዊ ምሁር ነው፡፡ እንደሱ ያሉ ሙሉ ሊቆች ጥቂትና አንዳንዴም የሚተኩ የማይመስሉ ክስተቶች ናቸው፡፡ አንዱ ሰው ብዙ ሰው ቢጠራቀም ቅርጭምጭሚቱ ጋር የማይደርስ ልሂቅ ነው፡፡ ይሄ ትውልድ ያሻውን ይሰድባል በዚሁ መንደር እንኳን ፕሮፌሰር መስፍን እስኪበቃቸው ተብጠልጥለዋል፡፡ በሰሞነኛ ጉዳይ ተራው የአንድርያስ እሸቴ ሆነ፡፡ የሰፈር ምሁር ባለመሆኑ የሰውዬው በሰፈሩ አለመከበር ለውጥ አያመጣል፡፡

በፕሮፌሰሩ ሀሳብ አለመስማማት፣ ሀሳቡን አለመውደድና ከሀሳቡ መቃረን ወንጀልም ነውርም አይደለም፡፡ እንዲህ ያሉ ምሁራን መንጋ የሚሞቃቸው የጭርታ ብርድ የሚጨወትባቸው ፈሬዎች ስላልሆኑ በሀሳባቸው ተቀባይ መጣትን አንዳንዴም እንደ ሀሳቡ ከፍታ ይመለከቱታል፡፡

እዚህ ሀገር ችግሩ እሱ አይደለም፤ ለዓለም የተፈፈውን ሰው ለራሱ መሆን ያቃተው ይዘልፈዋል፡፡ ብልጽግና የሚከበር ስራ ሰርቷል፡፡ አንድርያስን የሚያህል ሰው እያለ በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ሀሳብህ ምንድን ነው ብሎ አለመጠየቅ ኪሳራ ነበር፤ ሀሳብ የማይፈራው ፓርቲ ፕሮፌሰሩን ወደ ሀሳብ መድረኩ አምጥቷል፡፡ ትናንት ይሄ አይታሰብም፤ ተቃራኒ ሀሳብ ያለው ሰው የበይ ተመልካች በሀገሩ ምን ያገባዋል የሚባል ባዕድ ነበር፡፡

አንድርያስ ያለውን ለመረዳትም ሌላ እውቀት ይፈልጋል፡፡ ሰውዬው መምህር ቢሆንም ሶስተኛ ዲግሪ ሲያስተምር የኖረ በመሆኑ በቀላሉ ከስምንተኛ ክፍል ጋር በሀሳቡም በፍልስፍናውም ይግባባል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡

በሌላ በኩል እሱን ማብጠልጠል ፌስ ቡኩ ላይ ቀላል ነው፡፡ እንደ እሱ ዓለም ያጨበጨበለት ጆርናል ላይ አያሌ ጽሁፎችን ማሳትም፣ ጥልቅ ሀሳቦችን ማንሳት፣ በእውቀት መሞገት ለዚህ ትውልድ ዳገት ነው፡፡ ፕሮፌሰር አንድርያስ በዚያ ትውልድ ራሱ የሚከበር ስሙ ከፍ ያለ ሰው፡፡

ለማነኛውም ትውልድ የሚያጫርስ ብሔር ያሰከረው ዓለም አቀፋዊ ተንታኝ ሚዲያውንም፣ ፖለቲካውንም ትውልዱንም አርአያነቱንም ይዞ እንደ አንድርያስ እሸቴ ያለው ሰው ቢጥላላ አይገርምም፡፡ አንድርያስን ለማክበር እወቁት ብሎ ለዚህ እውቀት ምን ያደርጋል ባይ መንጋ ምክር ጉንጭ ማልፋት ነው፡፡ የየብሔራችሁን ምሁራን ጠይቋቸው እነሱ የሰውዬውን ልክ ይነግሯችኋል ማለቱ ይበቃል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top