Connect with us

የትግራይ ክልል ዜጎች በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ታፍነዋል አለ

የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ዜጎች ወደ ትግራይ በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ታፍነዋል አለ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የትግራይ ክልል ዜጎች በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ ታፍነዋል አለ

በመቐለ ከተማ ለሚካሄደውን የኢትዮጵያ የፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት መድረክ ለመሳተፍ ለጉዞ ሲዘጋጁ ከነበሩትን የጥምረቱ ኣባላት /5ት ሊቃነ መናብርት (ማለትም አቶ ገብሩ በርሀ፣ ልጅ መስፍን ሽፈራው፣ አቶ ተሻገር አረጋ፣ ወ/ሪት መዲና ኢማም፣ አቶ ጉዑሽ ገ/ስላሴ) ግንቦት 7/09/2012 ሰምንት ሰዓት ተኩል ገደማ በቦሌ ኤርፖርት የኮረና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል በሚል ሽፋን ወደ መቐለ ከሚበሩበት አውሮፕላን ታፍነው ከተወሰዱ በኃደለ ታስረዉ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ዓብዲ ዑመርና አባስ ሐጂ መሐመድ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ከመንገድ እንዲታፈኑ ተደርጓል፡፡

ይህ ድርጊት የሚያሳይው ሥርዓቱን እየመራ ያለው ፌዴራል መንግስት ከዚህ ቀደም ከዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መርህ በተቃራኒው ዲፕሎማቶች ከአውሮፕላን እንዳወረደውና ኢንቨስተሮች ወደ መቐለ እንዳይሄዱ እንደከለከለው ሁሉ ዛሬም የኢትዮጵያ የፌደራሊሰት ኃይሎች ጥምረት አባል ፓርቲ አመራሮች በአንቀፅ 31 መሰረት የተከበረው ህገ መንግስታዊው የመደራጀት መብት፣ በአንቀፅ 17 መሰረት የነፃነት መብት፣ በአንቀፅ 18 መሰረት ኢ‐ሰብአዊ አያያዝ ስለ መከልከሉ የተከበረው መብት በመተላለፍ ከህግ ውጪ ቤተሰባቸውም ሆነ ዘመድ እንዳይጠይቁ ሆኖ ዓለምዓቀፍ ህግና ህገመንግስቱን ጥሷል።

በመሆኑም ፌዴራል መንግስት ድርጊቱን በተመለከተ ተገቢዉ የእርምት እርምጃ በመዉሰድ የታፈኑት/የታሰረቱ በአስቸካይ እንዲለቃቸዉና ዜጎች በነፃነት እንዳይንቀሳቀሱ እያደረሰባቸዉ ያለዉ ክልከላና አፈና እንድያቆም መላ የአገራችን ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ሕገ-መንግስቱ እንዲከበር የበከላቸዉ አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸዉ፡፡

የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

መቐለ

ጉንበት 9/2012 ዓ/ም

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top