Connect with us

የጦር መሳሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ያስገቡት ተከሳሾች ጉዳያቸውን ….

የጦር መሳሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ያስገቡት ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ውሳኔ ተሰጠ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የጦር መሳሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ያስገቡት ተከሳሾች ጉዳያቸውን ….

የጦር መሳሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ያስገቡት ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ውሳኔ ተሰጠ

ተከሳሽ መሀመድ ጀማል አራጋው፣ዘይኑ አህመድ ሙሀመድ፣ ሰይድ አህመድ ይማም፣ ሀጎስ አመሃ አረጋዊ፣ ሐይደር ኑርየ አገሽን፣ መሀመድ ሀሚድ ሙሀመድ፣ ፋጡማ አህመድ ሲራጅ፣ ሰይድ ሀሰን አህመድ የተባሉት ግለሰቦች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ) እና በ2012 ዓ.ም የወጣውን የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር1177/2012 አንቀፅ 4(1) እና 22(3) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች የተላለፉ በመሆኑ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ይታወሳል፡፡

ተከሳሾች ፈቃድ ሳይኖራቸው ከቱርክ ሀገር በሁለት ኮንቴይነር ተጭኖ በጅቡቲ ወደብ በኩል ሊበርቲ ሺፒንግ ኤንድ ሎጂስቲክስ ኤል ኤል ሲ /Liberty Shipping and Logestics LLC/ በተባለ ድርጅት አማካኝነት በኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሽፋን ወደ ኢትዮጵያ የገባውን 501 /አምስት መቶ አንድ/ ካርቶን ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ሞዴሉ 9 ሚ/ሜ EKOL P29 የሆነ የጦር መሳሪያ ለማዘዋወር፣ ለመግዛት፣ ለመሸጥ ወይም ለማጓጓዝ በማሰብ በፈጸሙት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር የተደረገ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለ7ኛ ተከሳሽ ፋጡማ አህመድ ሲራጅ ዋስትና በመፍቀድ ሌሎች ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ በማዘዝ በክስ መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 3 ቀን 2012 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

(የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top