Connect with us

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰው ልጆችን በህይወት ጠብቆ የማሻገር ቁልፍ ተልዕኮ ያነገበ ነው!”

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰው ልጆችን በህይወት ጠብቆ የማሻገር ቁልፍ ተልዕኮ ያነገበ ነው!"
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰው ልጆችን በህይወት ጠብቆ የማሻገር ቁልፍ ተልዕኮ ያነገበ ነው!”

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰው ልጆችን በህይወት ጠብቆ የማሻገር ቁልፍ ተልዕኮ ያነገበ ነው!” – ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን

የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል።

ብሔራዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ በምስል የተደገፈ ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን በኮቪድ~19 ወረርሽኝ አደጋ ምላሽ አሰጣጥ፥ በበረሃ አምበጣ ወረርሽኝ የአደጋ አዝማሚያ እና በመጪው ወራት የአየር ፀባይ ትንበያ ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የብሔራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ም.ጠ.ሚ/ር አቶ ደመቀ እንደተናገሩት፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎች ማጠናከር ተገቢ ነው ~ ብለዋል።

የኮቪድ~19 ወረርሽኝን ለመግታት መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ በማድረግ በወሰዳቸው ትርጉም አዘል እርምጃዎች የሚያበረታቱ ቢሆንም፤ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው መዘናጋት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በአፅንዖት ተናግረዋል።

#የአስቸኳይ_ጊዜ_አዋጁ የሰው ልጆችን በህይወት ጠብቆ የማሻገር ቁልፍ ተልዕኮ ያነገበ እንደሆነ በመጠቆም፤ የወረርሽኝን አሳሳቢነት የሚመጥን ማህበረሰብ~አቀፍ የባህሪ ለውጥ ማረጋገጥ እና የመከላከል ዝግጅቱን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የበርሃ አምበጣ ወረርሽኝ የአደጋ አዝማሚያ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እና የሚያስከትለውን ጉዳት ሊመክት የሚያስችል ቅንጅታዊ ርብርብ መድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በመጪው ወራት የአየር ፀባይ ትንበያ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በሃገሪቱ ሊከሰት የሚችል የጎርፍ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያግዙ የዝግጅት ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል።

የብሄራዊ ኮሚቴውን ቁልፍ ተልዕኮ በጋራ ከማስፈፀም ባሻገር አባላት በዘርፍ ርብርብ እና በመዋቅር ቅንጅት በሚመጋገብ አግባብ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የብሔራዊ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው፤ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በትኩረት እንደሚያስፈፅሙ አረጋግጠዋል።

(ም/ጠ/ሚ ድረገፅ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top