Connect with us

ትግራይ ምርጫ ቢደረግስ?

ትግራይ ምርጫ ቢደረግስ?
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ትግራይ ምርጫ ቢደረግስ?

ትግራይ ምርጫ ቢደረግስ?
ባንክ አልተዘረፈበት፣ ተማሪ አልታገተበት፣ እረኞች አልተገደሉበት፣ አመራሮች በታጣቂ አልታደኑበት? ኮሮናውን ተጠንቅቀን እናደርጋለን ካሉ በክልሉ ብቻ ምርጫ መደረጉ ችግሩ ምንድን ነው?

ከስናፍቅሽ አዲስ
ኮሮናው መጥቶ እንጂ ኮሮናው ባይከሰትም ኖሮ አንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢ ምርጫ ሊደረግበት የሚችል አይመስልም ነበር፤ የጠፋ ተማሪ አላገኘንም፤ እረኛ መስክ ውሎ ታግቶ ይቀራል፡፡ ባንክ ተዘረፈ የሚል ዜና መስማት ብርቅም አልነበረም፡፡

ወረርሺኙ ያደረሰው ስጋት ምርጫውን በወቅቱ ለማካሄድ ከባድ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ በብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ይሄ እውነት ነው፡፡ ምርጫን ማካሄዱ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ የወያኔ ቅጥረኛ ናት አትበሉኝ እንጂ በትግራይ ይሄ ስጋት አይደለም ከተባለ ክልላዊ ምርጫ በክልሉ ማድረግ ምን ችግር ያመጣል?

የትግራይ ክልል አንጻራዊ ሰላም ነው፡፡ አንጻራዊ በሆነ ሁኔታ ህግና ስርዓት የሚከበርበት የኢትዮጵያ አካባቢም ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት የተከሰቱ ችግሮችን ስንቆጥር ሰው በቆንጨራ የተጨፈጨፈው እዚያ አይደለም፤ ሚሊዮኖች የተሰደዱት እዚያ አይደለም፤ ሌላው ቀርቶ ለጥናት የሄዱ እጩ ዶክተሮች ሊያመክኑን መጡ ተብሎ የተወገበትን ስናስብ፤ ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮአቸው ድረስ የተገደሉበት ችግር ስንቆጥር ትግራይ በወቅታዊው ሚዛን ለኢትዮጵያ እጅግ የተሻለችው ህግ የሰፈነባት ክልል መሆኗን እናያለን፤
ምርጫ ቦርድ በመላ ኢትዮጵያ ምርጫውን በወቅቱ ለማካሄድ እቸገራለሁ ብሏል፤ ልክ ነው ብዙ ሁኔታዎች እንዲህ እንዲወስን አስገዳጅ ናቸው፡፡

ትግራይ ግን ከዚህ በተቃራኒው እንችላለን የሚል የክልል መንግስት ካላት ምርጫ ቦርድ ትግራይ ክልል ገብቶ ምርጫውን በክልል ደረጃ ቢያስፈጽም ምን ችግር ይፈጠራል?

አንዳንድ የምንካረርባቸው ጉዳዮች ሌላ ትውልድ ጋር ቢደርሱ የሚያስተዛዝቡ ናቸው፡፡ ጓድ ሊቀመንበር ከወንበዴ አልደራደርም ያሉበት መንፈስ ዛሬ በሰው ሀገር የአረጋዊ ስደተኛ አደረጋቸው እንጂ ሀገራቸውን እንደ ምኞታቸው መች ታደገ?

የትግራይን የምርጫ ጉዳይ አለቅጥ ማክረሩና ግርግሩን ማድመቁ ለሀገር የሚበጅ አልመሰለኝም፤ ክልሉ እችላለሁ ካለ ምርጫ ያድርግ፤ ህዝቡ መርጦ ይመራ፤ አስጊ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫው እንደተባለው ተላልፎ ይካሄድ፤ የጨዋ ሀሳብ ሰንዝሩ፤

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top