Connect with us

የኮሮና ሪፖርት

የኮሮና ሪፖርት
Photo: Social media

ጤና

የኮሮና ሪፖርት

የኢትዮጵያ ከተገለጸ በኋላ በትግራይ ክልል የሚለው ሌላ መግለጫ ችግሩ የማንም ይሁን ያልተገባ ልምምድ ነው፡፡ ሀገር ነን፤ ለህዝብ ክብር ስትሉ ተቀናጁ፡፡
******
ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

የኮሮና ጉዳይ ሀገራዊ ብቻ አይደለም እንደውም በዓለም ደረጃ የዓለም የጤና ድርጅት ምድርን የተመለከተ አቃፊ ሀሳቦች መረጃዎችና ጉዳዮችን እውን የሚያደርግበት የምድር ቀውስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ መረጃዎችን ብሔራዊ በሆኑ ተቋማት በኩል ስትሰጥ ቆይታለች፡፡ ዘግይተውም ቢሆን ክልሎች የጀመሩት የምርመራ ስራ ውጤቱ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ተቀናጅቶ በጤና ሚኒስትር በኩል ሲነገር ቆይቷል፡፡

አሁንም ቢሆን የሁሉም ክልሎች ውጤትና የኮሮና ወቅታዊ ሁኔታ በማዕከላዊነት በጤና ሚኒስትር በኩል እየተገለጸ ነው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ግን የኢትዮጵያ የሃያ አራት ሰዓት መረጃ ይፋ ከሆነ በኋላ የትግራይ በሚል ሌላ ቁጥር ተነግሯል፡፡

ይሄ ፖለቲካ አይደለም፤ የሰው ህይወትና የሀገር ትርጉም ነው፡፡ ችግሩ ከየቱም ወገን ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለ ቆሻሻ ልምምድ ግን በኢትዮጵያ ምድር ሊኖር አይገባም፡፡ ይሄንን እንደ ህዝብ ልንቆጣው ይገባናል ምክንያቱም ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡

ውጤቱ ሳይደርስ የትግራይ ሪፖርት የሚዘገይበት አግባብ ካለ የፌዴራሉን ሪፖርት አዘግይቶ የሃያ አራት ሰዓቱን ሪፖርት አንድ ላይ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ አሊያ ደግሞ ሁሉም ክልሎች በራሳቸው ሚዲያና አግባብ መረጃውን እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡ ኢትዮጵያና ትግራይ ማለት ምን አገባኝ ባይነት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ነውርም ጭምር፤

ትግራይ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንዲህ ያሉ ልምምዶች ፖለቲከኞችን ያሰክራሉ፤ ክፉና ስውር ደባ ያላቸው ሰዎች ልምምዱን ወደ መጥፎ ልዩነት ይዘውት ይጓዛሉ፡፡ በትግራይ የሚደረገው የማዕከላዊ መንግስቱ ኮሮናን የመከላከል እንቅስቃሴ ሊሽኮረመም አይገባውም፡፡ እንደሌላው አካባቢ ሁሉ በትግራይም ኮሮናን ለመከላከል የሚሰራው ስራ በፌዴራል መንግስቱ በአግባቡ ሊታገዝ ይገባዋል፡፡ ከዚያ ውጪ የቱም ወገን አሳስቆ የጥፋት ቢያቆም መልካም ይመስለኛል፡፡ ህዝቡ ይከበር፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top