Connect with us

ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የኢዴፓ እና የፓርላማ አባል – ለልደቱ አያሌው

ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የኢዴፓ እና የፓርላማ አባል - ለልደቱ አያሌው
Photo: Social media

ፓለቲካ

ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የኢዴፓ እና የፓርላማ አባል – ለልደቱ አያሌው

ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የኢዴፓ እና የፓርላማ አባል – ለልደቱ አያሌው

ልደቱ ሆይ! ማንኛውንም አምባገነን እንደማልታገስ ሁሉ ዓይኔ እያየ ሀገሬን ስታፈርስ ዝም አልልህም! ዱሮም ስታገልህ ነበር አሁንም ትግሌን እቀጥላለሁ!

በነገራችን ላይ ልደቱ ዱሮም ኢዴፓን አያውቀውም፡፡ ሲጀመር የመዐህድ አባል ነበር፡፡ እንደ አስተሳሰብ የሊበራሊዝምን ፍልስፍና “የጫንበት” ኢዴፓ ሲመሰረት እዚያ የነበርን (ከመዐህድ ያልመጣን) አባላት ነበርን፡፡ እኛ (ብዙዎቻችን) ከአካባቢው ስንጠፋ እነሆ ልደቱ ወደነበረበት መርህ ዐልባ አረንቋ ተመለሰና ያገኘውን ፈረስ መጋለብ ጀመረ… እናም ሰሞኑን ልደቱ እያራገበው ያለው ሃሳብ በመዐህድ መንፈስ ውስጥ ሆኖ ነው እንጂ በኢዴፓ መንፈስ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡

ለመሆኑ ልደቱ የሰሞኑን አስተሳሰቡን እያራመደ ያለው እንደ ግለሰብ ነው ወይስ እንደ ኢዴፓ? ያን ሃሳብ እንደ ኢዴፓ እንዲያራግብ የፈቀደለት የትኛው የፓርቲው አካል ነው? ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ነው ወይስ አቶ ልደቱ?

ትግሉን ገና ጀመርኩት፡፡ ልደቱ እርቃኑን እስኪቀር ትግሉ ይጥላል!

ክቡራትና ክቡራን የኢዴፓ አባላት ሆይ! ለእናንተ ያለኝ አክብሮት እንደ ጸና ነው! ከኢዴፓ ጋር ጠብ የለኝም፡፡ ልደቱ ግን መስመር ስቷል፡፡ ከኢዴፓ የምክንያታዊነት ሐዲድ ወጥቷል፡፡ ልደቱን ወደ መስመሩ በመመለሱ ሂደት አብረን እንታገል ጥሪዬ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top