Connect with us

ፓርላማው መጪውን ምርጫ በማራዘም ጉዳይ ነገ ይወስናል

ፓርላማው መጪውን ምርጫ በማራዘም ጉዳይ ነገ ይወስናል
Photo Facebook

ዜና

ፓርላማው መጪውን ምርጫ በማራዘም ጉዳይ ነገ ይወስናል

ፓርላማው መጪውን ምርጫ በማራዘም ጉዳይ ነገ ይወስናል

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሚያዝያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሄዳል፡፡

ም/ቤቱ ነገ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን በተመለከተ የቀረቡ የመፍትሄ አማራጮችን የውሳኔ ሃሳብ እና ስድስት የብድር ስምምነቶችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባው ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን በተመለከተ የቀረቡትን የመፍትሄ አማራጮችን መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ መመራቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ምርጫን በተመለከተ ከቀረቡ አራት የመፍትሄ አማራጮች መካከል ቋሚ ኮሚቴው ምርምሮ የሚያቀርበው የውሳኔ ሃሳብ ነገ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top