Connect with us

ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል

ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል
Photo: Reporter

ኢኮኖሚ

ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል

ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 26 ቀን 2012 (ንኢሚ) አስገዳጅ የኢትዮጵያ የጥራት ደረጃ ያላሟሉ ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለፉት 9 ወራት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ምርቶች ላይ ባካሄደው የጥራት ቁጥጥር ከ2500 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆኑት ከደረጃ በታች በመሆናቸው ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል፡፡

በቁጥጥሩ ከታገዱት የገቢ ምርቶች 2304.95 ሜ.ቶ ጥቅል ብረት፣ 28.7 ሜ.ቶ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣180 ካርቶን ሳሙና፣ 142 ካርቶን በፀሐይ ብርሀን የሚሰራ የእጅ ባትሪ፣150 ካርቶን የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲሁም 43.22ሜ.ቶ የቆርቆሮ መስሪያ ጥሬ እቃ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም 272 ጥቅል የአርማታ ብረት፣19770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት፣2934 ፍሬ የዉሃ ፓምፕ፣ 875 ካርቶን ባትሪ ድንጋይ አንዲሁም የታሸጉ ምግቦችና ሌሎችም የገቢ ምርቶች በቁጥጥሩ ወቅት ከጥራት መስፈርት በታቸ ሆነው በመገኘታቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ እንዳይገቡ የተደረጉ ሲሆን በተደረገውም ቁጥጥር ምርቶቹ ሀገር ውስጥ ቢገቡ በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የጤና፣ የደህንነትና የጥቅም ጉዳት ማስቀረት ተችሏለል፡፡

(ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top