Connect with us

ከድሬዳዋ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

ከድሬዳዋ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ከድሬዳዋ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

ሚያዚያ 24/2012 ዓ.ም. ጠዋት ረፋድ ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ አዲሱ ኬላ በሚባለው አካባቢ ከህብረተሰቡ ስለኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በተሰጠው ጥቆማ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምስራቅ ኢትዮጵያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ በቦታው ተገኝቶ ህግ በማስከበር ላይ እያለ በተፈጠረ ችግር የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በአራት ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።

የድሬዳዋ አስተዳደርም የተፈጠረውን ችግር መንስኤና ዝርዝር ሁኔታውን የሚያጣራ ቡድን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ከፌደራል ፖሊስና ከድሬዳዋ ፖሊስ ኮምሽን አዋቅሮ ወደ ስራ አስገብቷል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ አስፈላጊውን መረጃ ለግብረ ሃይሉ በመስጠት የተለመደ ቀና ትብብሩን እንዲያደርግ አስተዳደሩ እየጠየቀ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ለህብረተሰባችን ለመግለፅ እንወዳለን።

በመጨረሻም ለጠፋው የሰው ህይወትና ለደረሰው የአካል ጉዳት አስተዳደሩ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በቀጣይም የተቋቋመው ግብረ ሃይል በሚያደርገው ማጣራት ላይ ተመስርቶ የሚደርስበትን ውጤት ለህብረተሰቡ በይፋ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የድሬዳዋ አስተዳደር
ሚያዚያ 24/2012 ዓ.ም.
ድሬዳዋ/ኢትዮጵያ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top