Connect with us

ሕገወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሀኒት አዘዋዋሪዎች ተያዙ

ሕገወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሀኒት አዘዋዋሪዎች ተያዙ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ሕገወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሀኒት አዘዋዋሪዎች ተያዙ

ሕገወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሀኒት አዘዋዋሪዎች ተያዙ

2 ነጥብ 4 ሚልዮን ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 ለመከላከል ያገለግላሉ የተባሉ ህገ-ወጥ የፊት ጭንብል(face mask) እና ህገ-ወጥ ለስንፈተ ወሲብ የሚያገለግል በማለት(Vimax herbal supplement) አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሚያዚያ 23/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቀጥጥር ባለስልጣን አስፈላጊዉን ጥናት ካጠናቀቀ በኋላ ከአዲስ አበባ ፖሊሥ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ህገ-ወጥ ዝውውር ላይ ባከናወነው ኦፕሬሽን

1ኛ. መስቀል ፍላወር አካባቢ በተሽከርካሪ የፊት ጭንብል(N95 face mask) ብዛት 15,000 እና 05 የሙቀት መለኪያ ቴርሞ ሜትር/Infrared thermometer እና ፒያሣ አካባቢ Surgical face mask ብዛት 1,000 የሆነ በህገ-ወጥ መንገድ ለህገወጦች ሊሸጥ ሲል ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር ስምንት ግለሰቦች እጅ ከፈንጅ ተይዘው ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።

2ኛ. Vimax herbal supplement የተባለ በባለሥልጣኑ ያልተመዘገበና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ ህገ-ወጥ ምርት ለስንፈተ ወሲብ የሚሆን በማለት በፌስቡክ ሲያስተዋዉቁ የነበሩ ግምቱ 17 ሺ 500 ብር የሆነ በአዲስ አበባ ሳሪስ አካባቢ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር አንድ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top