Connect with us

“ወ/ሮ ትዕግስት እንግሊዛዊት ናት፤ የኢትዮጵያ ዜግነት የላትም” ፖሊስ

"ወ/ሮ ትዕግስት እንግሊዛዊት ናት፤ የኢትዮጵያ ዜግነት የላትም" ፖሊስ
Photo: Social media

ህግና ስርዓት

“ወ/ሮ ትዕግስት እንግሊዛዊት ናት፤ የኢትዮጵያ ዜግነት የላትም” ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው ግለሰብ ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ራሷን ንግሥተ ነገሥት ብላ በምትጠራው እና የአራት ልጆች እናት በሆነችው እኅተ ማርያም ላይ ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።

ከሁለት ዓመት በፊት ባሏ በሞት የተለያት የ43 ዓመቷ እኅተ ማርያም በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ሴት ስለ ማንነቷ ለፖሊስ ስትገልጽ፣ ትክክለኛ መጠሪያ ስሟ ትዕግሥት ፍትሕአወቀ አበበ መሆኑንና መኖሪያዋ ኮልፌ መብራት ኃይል አካባቢ እንደሆነ ተናግራለች።

ግለሰቧ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ በመኖሪያ ቤቷ በሃይማኖት እና በምገባ ስም እስከ መቶ የሚደርሱ ሰዎችን ሰብስባ በመገኘቷ በቁጥጥር መዋሏ ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ፣ ልዩ ምወንጀሎች ምርመራ ዲቪን ሓላፊ ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ግርማ፣ ተጠርጣሪዋ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ኮሮናቫይረስ የለም ተሳሳሙ፣ ተቃቀፉ፣ ተጨባበጡ በማለት አዋጁን በመፃረር የዜጎችን ሕይወት ለአደጋ አጋልጣለች በሚል መጠርጠሯን ገልጸዋል።

ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የተጠረጠረችበት ወንጀል ጉዳይ እየታየ መሆኑንም ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዋ በ2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መሀል ላይ የሚገኘውን ኮከብ ቀድዳ አውጥታ በማቃጠሏ መቀጣቷም ተጠቅሷል።

ግለሰቧ ከሰማይ ታዝዤያለሁ በማለት ማረሚያ ቤት ድረስ በማቅናት ታራሚዎችን ልታስወጣ ስትሞክር እጅ ከፍንጅ ተይዛ መቀጣቷንም ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።

ከትላንት በስቲያ ማምሻውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋ በቁጥጥር ስር ስትውል አብረው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ የመጡ 30 የሚጠጉ ተከታዮቿ ግርግር ሊፈጥሩ ቢሞክሩም ፖሊስ መክሮ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉንም አመልክተዋል።
ከእርሷ ጋር በግብረ አበርነት የተጠረጠሩ ሁለት ሴቶች ግን ምርመራ እየተካሔደባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር በድሉ ተናግረዋል።

ግለሰቧ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ክሕደት ቃል በሳይንስ እንደማታን፣ ርትዕት ተዋሕዶ የተሰኘ ሃይማኖት ለማስተማር ከሰማይ እንደተላከች እና ራሷም ንግሥተ ነገሥት ዘኢትዮጵያ መሆኗን ተናግራለች።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top