Connect with us

ዑመር ሰመተር-የምሥራቁ ኮኮብ

ዑመር ሰመተር-የምሥራቁ ኮኮብ

ባህልና ታሪክ

ዑመር ሰመተር-የምሥራቁ ኮኮብ

ዑመር ሰመተር-የምሥራቁ ኮኮብ፤
አባት አርበኞችን የመዘከር ጉዞ

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ታላቁን ደጃዝማች ዑመር ሰመተርን ሊያስታውሰን ነው፡፡ ሚያዚያ 27ን ምክንያት በማድረግ የአባት አርበኞች ዝክር ትረካው ቀጥሏል፡፡ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ይኼ ስም የድል ምሳሌ ነው፡፡ ይኼ ስም የኢትዮጵያ ባህውርታዊነትና የወል የድል ታሪኳ ማሳያ ነው፡፡ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር፡፡ ከዛሬ 140 ዓመት በፊት ካልካዮ በተባለ ቦታ ተወለዱ፡፡ ዑመር ሰመተር በባህላዊው አስተዳደርም የአካባቢ ገዥ የነበሩ የጎሳ መሪ ነበሩ፡፡

ሀገር የወልወሉ ግጭት ብላ ከምትጠራው የታሪክ ክስተት ጀርባ አንድ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጀግና አሉ፡፡ ዑመር ሰመተር፤ ወልወል ጣሊያን በጎንደር በኩል ከተነኮሰችው ግጭት በኋላ በስምንተኛው ወር በህዳር 26 ቀን 1927 ዓ.ም. ነው፡፡

ካፒቴን ቺማሩታ ይባላል የጠቡ ተንኳሽ የኢጣሊያ ሰው፡፡ በወልወል በኩል የሀገር መሬት ይዞ አልለቅም በማለቱ በስፍራው በነበሩት በፊታውራሪ ሽፈራና በፊታውራሪ አለማየሁ ላይ አደጋ ጣለ፡፡ በአየር ጭምር ውጊያ ገጠመ፡፡

በጦርነቱ በብርቱዎቹ የሀገር ልጆች ቢቀምስም ድንበር ጥሶ እንደገባ አልኾነም፡፡ ቢወቀስ ያቀረበው ድርድር ከባድ ኾነ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት 2 መቶ ሺህ ብር ካሳ ይስጠኝ አለ፡፡ አልበቃውም፤ ሌላ ተመኘ፡፡

ምኞቱ የኢትዮጵያ መንግስት ዑመር ሰመተርን ይዞ እንዲሰጠው የሚሻ ሆነ፡፡ ዑመር ሰመተር እንዲህ ያለው የጣላት ምኞት ነበር፡፡ ደጃዝማች ዑመር ድንቅ አርበኝነት ታሪክ ያላቸው የምስራቅ ኢትዮጵያ የታላቁ ሀገር ጌጥ የኢትዮጵያ ኩራት ነበሩ፡፡

ዑመር ሰመተር ደጃዝማች ያደረሳቸው ክብር ለሀገር የከፈሉት ታላቅ ተጋድሎ ነው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ በዚሁ ምክንያት ደጃዝማች ብለው በኡጋዴንና ጅግጅጋ ላይ በገዢነት ሾመዋቸዋል፡፡ ለሀገር ሲሉ በዋሉበት የጦር አውድ ወደ ሰውነታቸው የገባች ጥይት ውላ አድራ መረቀዘች፡፡ እሳቸው ሲቆስሉ ደጃዝማች አፈወርቅ የተባሉ ጀግና ደግሞ በዚሁ ውጊያ ተሰውተው ነበር፡፡

በገርለጉቤ፣ በቆራሂና በሃነሌ የተዋደቁት አርበኛ መጋቢት ስድስት ቀን 1936 ስደት አብሮ ከተሰደደ ሰውነት ውስጥ የገባ ጥይት ጋር ታግለው በተፈጠረ ህመም ሳቢያ የጀግና ሞት ሞቱ፡፡ የ65 ዓመቱ ጀግና ስማቸው ከኢትዮጵያ አይደፈሬነት ጋር ታትሞ ቀረ፡፡ ደጃዝማች ኡመር ሰመተር፤

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top