Connect with us

“በጃንሜዳው ግጭት የሞተ ሰው የለም” ፖሊስ

"በጃንሜዳው ግጭት የሞተ ሰው የለም" ፖሊስ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

“በጃንሜዳው ግጭት የሞተ ሰው የለም” ፖሊስ

“በጃንሜዳው ግጭት የሞተ ሰው የለም” ፖሊስ

በጃን ሜዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግርግር በስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ላይ መካከለኛ ጉዳት መድረሱንና ጉዳቱ የተከሰተው በመገፋፋት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ግብይቱ በመደበኛ ሁኔታ መካሄዱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ለመከላከል እንዲረዳ ታስቦ ፒያሳ አትክልት ተራ የነበረው የአትክልት እና የፍራፍሬ ግብይት ወደ ጃን-ሜዳ እንዲዛወር መደረጉ ይታወሳል፡፡

በጃን ሜዳ የሚደረገው ግብይት ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት አጋላጭ እንዳይሆን ልዩ ልዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በተለይ የንግዱ ስርዓት ህጋዊ ሥርዓቱን መንገዱን ተከትሎ እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከደንብ ማስከበር አገልግሎት እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳ ለሚያዚያ 21 ቀን 2012 ዓ/ም ጠዋት ግብይቱ በመከናወን ላይ እንዳለ ከጠዋቱ 2፡ 30 አንዳንድ ግለሰቦች ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ መገፋፋት ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ላይ መካከለኛ ጉዳት ማጋጠሙን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሰለሞን ገ/ማርያም ገልፀዋል፡፡ ከተጎጂዎቹ መካካል ስድስቱ ህክምና አግኝተው ከሆስፒታሉ መወጣታቸውንና አንደኛው ተጎጂ ህክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

በአካባቢው በተፈጠረው ግርግር ሁለት ሰዎች ሞተዋል ተብሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ ተናግረው ፖሊስ አጋጥሞ የነበረውን እረብሻ በቀላሉ ተቆጣጥሮ ግብይቱ እንዲቀጥል ማድረጉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡(የፌ/ፖ/ኮምሽን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top