Connect with us

አየር መንገዱ የገጠመውን ኪሳራ ለማካካስ የጭነትና የጥገና አገልግሎቱን እያስፋፋ መሆኑን ገለፀ

አየር መንገዱ የገጠመውን ኪሳራ ለማካካስ የጭነትና የጥገና አገልግሎቱን እያስፋፋ መሆኑን ገለፀ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

አየር መንገዱ የገጠመውን ኪሳራ ለማካካስ የጭነትና የጥገና አገልግሎቱን እያስፋፋ መሆኑን ገለፀ

አየር መንገዱ የገጠመውን ኪሳራ ለማካካስ የጭነትና የጥገና አገልግሎቱን እያስፋፋ መሆኑን ገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮኖና ቫይረስ ምክንያት በመንገደኞች ማጓጓዝ አገልግሎት የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ የጭነትና ጥገና አገልግሎቶች ላይ በስፋት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገድ ከቻይናዊ ባለጸጋ ጃክ ማ ለ54 አፍሪካ አገራት ለሦስተኛ ዙር ያደረጉትን አይነተ ብዙ የሕክምና ግብዓቶች  አዲስ አበባ ማስጋበት ጀምሯል።

ከትናንት ጀምሮ ሰሞኑን በሦስት ዙር የሚያስገባቸው የሕክም ግብዓቶች ለ54ቱ የአፍሪካ አገራት የሚዳረስ 61 ሺህ ኪሎ ግራም የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ሲሆን ከዚህ በፊትም በመጀመሪያው ዙር 100 ሺህ ኪሎ ግራም፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ 160 ሺህ ኪሎ ግራም አጓጉዟል።

ትናንት ማጓጓዝ ከጀመራቸው ቁሳቁስ መካከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ መመርመሪያዎች፣ የመተንፈሻ መሳሪያዎች፣ የሕክምና አልባሳትና የፊት መሸፈኛዎች፣ የሙቀት መለኪያዎችና 500 ሺህ ጥንድ የእጅ ጓንቶች ይገኙበታል።

የአየር መንገዱ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍጹም አባዲ እንዳሉት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ የአየር መንገዱ 90 አውሮፕላኖቹ ሥራ በማቆማቸው በገቢው ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

ከ80 በመቶ በላይ ገቢው በመንገደኞች ማጓጓዝ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ እንደነበረ ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ የካርጎና የጥገና አገልግሎቱን በሦስት እጥፍ በማሳደግ የሚደርስበውን ኪሳራ ለመቋቋም እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

አየር መንገዱ ከአፍሪካ አገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅና እስያ አገራት በማጓጓዝ ላይ መሆኑም ገልጸዋል።

ከአፍሪካ ውጭ ባሉ ሌሎች አገራትም ሲመለስም የተለያዩ የንግድ ዕቃዎችንና የሕክምና ግብዓቶችን በማጓጓዝ በጥሩ ደረጃ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

አየር መንገዱ በሚሰጠው አገልግሎት ብቃትና ጥራት የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና አገራት ጭምር ተመራጭ የካርጎ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት እንዳደረገው ገልጸዋል።

ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙም ሆነ ሌሎች የንግድ የጭነት አገልግሎቱን ከአፍሪካ አገራት ባለፈ በሌሎች ክፍላተ ዓለማት ሁሉ እያሰፋ መሆኑን ተናግረዋል።

ለጃክ ማ የሕክምና ግብዓቶች ለማከፋፈልም የተመረጠበትም ግለሰቡ የአየር መንገዱ ያለውን አገልግሎት ተመልክተው መሆኑን ጠቁመዋል።

አየር መንገዱ ከ80 በመቶ በላይ ገቢውን የሚያመነጨው መንግደኞችን በማጓጓዝ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ኪሳራውን ባይሸፍንም እንኳ በካርጎና ጥገና አገልግሎቱ የሚደርስበትን ኪሰራ ለማካካስ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሆነም ነው አቶ ፍጹም ያብራሩት።

ለዚህም የመንገደኞችን አውሮፕላኖች ለጭነት አገልግሎት የማሰማራት ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢዜአ  ሚያዚያ 19/2012

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top