Connect with us

ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር

ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር

ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር

የወ/ት ኤልሳቤጥ ከበደ የፍ/ቤት ሂደት ስለማሳወቅ

• የማህበራችን አባል እና በጎ ፈቃደኛ ወ/ት ኤልሳቤጥ ከበደ ከአዲስ አበባ ወደ ሀረሪ ክልል በቀን 27/7/2012 ዓ.ም እንድትወሰድ መደረጉን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጡን በቀን 29/7/2012ዓ.ም በደብዳቤ.ቁ EWLA/6499/12 የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡

• ይህ በእንዲህ እንዳለ ወ/ት ኤልሳቤጥ በተጠረጠረችበት ወንጀል በሀረሪ ክልል ከፍተኛው ፍ.ቤት እየተከታተለች የምትገኝ ሲሆን የተጠረጠረችበት ወንጀል ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተገናኘ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና በምታሰራጨው ሀሰተኛ ጽሁፎች ብሄር ከብሄር እና ሀይማኖት ከሀይማኖት በማጋጨት የሚሉ መሆናቸው እንደተገለጸላት ለማወቅ ችለናል፡፡፡

• ወ/ት ኤልሳቤጥ የተጠረጠረችበት በወንጀል ህግ ስነ ስርአት መሰረት በሀረሪ ክልል ፍ/ቤት ስልጣን ስር የማይወድቅ በመሆኑ ፍ/ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ እንዲያሰናብታት ብትጠይቅም በችሎቱ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን፣ ከዚህም በላይ ወ/ት ኤልሳቤጥ በፍ/ቤት ከነበሩት አራት ቀጠሮዎች ውስጥ በሁለቱ እንድትቀርብ ሳይደረግ በሌለችበት መዝግቡ መታየቱን ቤተሰቦችዋ ገልጸዋል፡፡

• ጉዳዩ አሁን ባለበት የምርመራ ደረጃ ላይ በህግ ስልጣን ከተሰጠው ፖሊስ የምዝገባ መዝገቡን አደራጅቶ ሳያጠናቅቅ ከፖሊሱ በተጨማሪ አቃቤ ሀግ በመዝገቡ ክስ ሳይመሰረት በፊት ፍ/ቤት ቸሎት በመቅረብ ክርክር እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን ምላሽ እንዲሰጥም በፍ/ቤቱ ዳኛ አድል እየተሰጠው እንደሚገኝ ፍ/ቤቱ ከሰጠው ትእዛዝ ለመረዳት ችለናል፡፡

• ዋስትናን በተመለከተ ምርመራው ሳያልቅ በዋስ ብትለቀቅ መረጃ ታጠፋለች በማለት ወ/ሪት ኤልሳቤጥ የዋስትና መብትዋ እንዲከበር ያቀረበችውን ጥያቄ ባለመቀበል ፍ/ቤቱ ጊዜ ቀጠሮ እስከ 26/08/2012 ፈቅዷል፡፡ በድጋሚ ከዋስትናው ጋር በተገናኘ ፍ/ቤቱ ለ29/8/2012 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ግልጽ ባለመሆኑ ማህበራችን ይህንኑ እያጣራ ይገኛል፡፡ ሆኖም መረጃ በቀላሉ ከፌስቡክ ገጽዋ ላይ በሰአታት ፖሊስ መሰብሰብ ይችላል፡፡

• የወ/ት ኤልሳቤጥን ጉዳይ እየታየ ያለው በሀረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደመሆኑ ተቋማችን ወ/ት ኤልሳቤጥ ትክክለኛ ፍትህን ለማግኘት እንድትችል ጠበቃ ለመወከል ጥረት እያደረገ ቢሆንም ያነጋገርናቸው የክልሉ የጥብቅና ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎች ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ጉዳዩን ለመያዝ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ከክልሉ የተገኙ ተመደበው የነበሩት ጠበቃም የዋስትና አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረቡ በኋላ በግል ምክንያት መቀጠል እንደማይችሉ ገልጸው አቋርጠውታል፡፡

ማህበራችን የወ/ሪት ኤልሳቤጥን ጉዳይ እስከመጨረሻው ከሚመለከታቸው የመንግስት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር በመስራት ተገቢውን ፍትህ የማሰጠት ስራችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እንዲሁም በቀጣይ ያሉ የፍርድ ሂደቶችንም እንደምናሳውቅ እንገልፃለን፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top