Connect with us

የአምላክ ሥራ

የአምላክ ሥራ
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

የአምላክ ሥራ

የአምላክ ሥራ
ኘሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

እናቴን ከየጁ አባቴን ከአንኮበር አምጥቶ በስድስት ኪሎ አካባቢ እኔን ከፈጠረኝ ዘጠና ዓመታት አለፉ! ዘጠና ዓመት! እናትና አባቴ አልደረሱበትም! እኔም አላሰብሁትም! ስለአንድ ሽማግሌ አንድ ግጥም ጽፌ ነበር፤

ቆሜ አየዋለሁ

ስጓዝ በጎዳና፣
አገኘሁ መንገደኛ፤
ዕድሜው ከናሳሩ፣
የሚታይ በግንባሩ፤
እንዴት ነው? አልሁተ መንገዱ፣
የመውጣት፣ የመውረዱ
ለኔ ከእንግዲህ ወዲያ ቁልቁለት ነው፤
መውረድ ብቻ ነው የቀረው፤
አንተ አፋፉን ካለፍከው
አይደክምህም ሌላው

ሊሄድ ሲል እንደገና
ጤቅሁት ‹‹ስንት አፋፍ አለ?››
እንደመንገድህ ነው አለ፤
እንደፍላጎትህ፣
ማንም አይከለክልህ፤
ታች ታቹን ከሄድክ አፋፍ አትወጣም፤
አፋፍ ከወጣህ መውረድ አይቀርም!
ሜዳ ሜዳውን ሰላም ነው፤

አፋፉ ላይ ነው ጭንቀት ያለው፤
እባክህ ምከረኝ፤
የትኛው መንገድ ነው የሚሻለኝ?
ብዬ ብጠይቀው፣
ጭንቀቱ ፊቱን ሞላው፤
መንገዳችን ለየቅል፣
አንተ ዳገቱን እኔ ቁልቁል፣
የኔ ላንተ አይሆንም፤
የሚሻልህን አላውቅም፤
አለኝና ቀጠለ ቁልቁለቱን፣
እኔም ቆሜ አየዋለሁ፤ አቀበቱነ!

ይኸው ዛሬም ቆሜ አየዋለሁ፤ አቀበቱን!

እግዚአብሔር ከብዙ ነገሮች፣ ከብዙ ችግሮች፣ ከብዙ አደጋዎች ሰውሮኛል፤ ክብርና ምስጋና ይድረሰው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰውን እንድወድ አድርጎኛል፤ ከምንም ነገር በላይ የሰው ፍቅር ሰጥቶኛል፤ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት ጥቂት ሰዎች፣ አሥር የማይሞሉ ሰዎች የሰጡኝ እርዳታ ኑሮዬን የጌታ ኑሮ አድርጎልኛል፤ በጡረታዬ ብጎዳም የሚጦሩኝ ሰዎች ስለሰጠኝ መድኃኔ ዓለምን በጣም አመሰግነዋለሁ፤ አልተቸገርሁም፤ እግዚአብሔር ለነዚህ ሰዎችም የሚያስብላቸው ይስጣቸው፤ ኑሯቸውን የተመቻቸ ያድርግላቸው፤ አብዝቶና አባዝቶ ይስጣቸው፤ ሁሌም ለሰው የሚተርፉ ያድርጋቸው!

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top