Connect with us

ኢትዮጵያ 35 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደልኩ አለች

ኢትዮጵያ 35 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደልኩ አለች
Photo Facebook

ማህበራዊ

ኢትዮጵያ 35 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደልኩ አለች

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ወስድኩት ባለው የተቀናጀ የማጥቃት እርምጃ 35 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድሎ 14 ማቁሰሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

አንደ ዘገባው የኢትዮጰያ መከላከያ ኃይል“በሶማሊያ ባይደዋ ለተሰማራው ሴክተር ሶስት የመከላከያ ሰራዊት የግዳጅ አፋፃፀም አስፈላጊ የሆኑ ንብረቶችን ከሶማሊያ እስከ ባይደዋ በኮንቮይ አማካኝነት ሲያጓጉዝ በነበረበት ሰአት አልሸባብ ማጥቀት ሲሞክር ነው በአልሸባብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አካባቢው አልሸባብ የሚንቀሳቀስበትና በተደጋጋሚ ጥቀት ለማድረስስ የሚሞክርበት በመሆኑ የኮንቮይ ጉዞውን በጥንቃቄ ለማከናወን ችሏል፡፡

አልሸባብ በኮንቮይ ጉዞ ለማደናቀፍ በሰራዊቱ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረው እንቅስቃሴ በፀረ ማጥቃት እንቅስቃሴ ከፍጸኛ ኪሳራ እንደደረሰበት መከላከያ አስታውቋል፡፡

በጥቃቱ ከሞቱት መካከል በፈንጅ አቀነባባሪነት የሚታወቀው ጀቢል የተባለው ግለስብ እንደሚገኝበት ዘገባው ጠቅሷል፡፡

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top