Connect with us

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የዋስትና መብት ተፈቀደለት

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የዋስትና መብት ተፈቀደለት

ህግና ስርዓት

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የዋስትና መብት ተፈቀደለት

ያየሰው ሽመልስ በተከሰሰበት የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ወንጀል በዛሬው እለት የ15 ሺህ ብር ዋስት በማቅረብ ውጭ ሆኖ ጉዳዩን እንዲከታተል ተወሰነ፡፡

ያየሰው ሽመልስ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት አዋጅን በመጣስ ወንጀል በትናንትናው እለት በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን የተከታተለው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ተከሳሽ በ15 ሺ ብር የዋስትና መብቱ ተፈቅዶ ጉዳዩን ውጭ ሆኖ እንዲከታተል የወሰነ ሲሆን የክስ መቃዋሚያ ለማቅረብና ለመጠባበቅ ለግንቦት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

(የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)


ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ተከሰሰ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት አዋጅ ጋር በተያያዘ በያየሰው ሽመልስ ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡

ተከሳሽ ያየሰው ሽመልስ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት አዋጅን በመጣስ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ወንጀል በዛሬው እለት ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሽ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀፅ 5 እና 7/4/ ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ ተከሶ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለልደታ ምድብ ችሎት ቀርቧል፣ ተከሳሽ መረጃዉ ሐሰት የሆነና የመረጃዉን ሐሰተኝነት እያወቀ ወይም ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንፃር የመረጃዉን እዉነተኝነት ለማጣራት በቂ ጥረት ሳያደርግ በቀን 17/07/2012 ዓ.ም ተከሳሽ ያየሰው ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ መንግስት 200 ሺህ መቃብር ለኮሮና ቫይረስ ሟቾች እንዲዘጋጅ ትእዛዝ የሰጠ በማስመሰል በራሱ ስም በሚጠቀመዉ የማህበራዊ ሚዲያ (ፌስ ቡክ ገጽ) አማካኝነት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑትን ፎቶግራፍ በመለጠፍ ”200ሺህ የመቃብር ቦታዎች እንዲዘጋጁ መንግስት አዘዘ” በማለት በፅሁፍ የሐሰት መረጃን ያሰራጨ በመሆኑ በፈፀመዉ የሐሰት መረጃን ማሰራጨት ወንጀል መከሰሱን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ተከሳሽ ከቀን 18/07/2012 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉ አዋጅ በህዝብ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል፡:

(ምንጭ:-የፌ/ጠ/ዐቃቤ ሕግ)

 

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top