በቻይና የሚገኝ አንድ የእግር ኳስ ክለብ የዓለማችን ትልቁን ስታዲየም ግንባታ ጀመረ
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትትን ሳቢያ ተጥለዉ የነበሩ እገዳዎች መነሳታቸዉን ተከትሎ በቻይና የሚገኝ አንድ የእግር ኳስ ክለብ የአለማችን ትልቁን ስታዲየም ሊገነባ መሆኑን ሲ.ኤን.ኤን ዘገበ፡፡
ጉዋንዙ ኤቨግራንዴ የተባለዉ ይህ የእግር ኳስ ክለብ 100 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችለዉን ግዙፍና እጅግ ቅንጡ ስታዲየም ለመገንባት ስራ መጀመሩን ክለቡ አስታዉቋል፡፡
በሎተስ ተብሎ በሚጠራዉ አበባ ቅርጽ ዲዛይን የተደረገዉን ይህንን ስታዲየም ለመገንባት 1.7 ቢሊየን ዶላር ወይንም 12 ቢሊየን የቻይና ዩኣን ወጪ እንደተደረገና በፈረንጆቹ 2022 ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ዘገባዉ አመልክቷል፡፡
ስታዲየሙ ሲዲኒ ዉስጥ እንደሚገኘዉ ኦፔራ ሀዉጂና አንደ ዱባዩ ቡርጂ ከሊፋ ከዓለማችን ድንቅ የመስብ ቦታዎች እንዱ ሆኖ እንዲጠራና የቻይና እግር ኳስ ምልክት እንዲሆን ታስቦ እንደሚሰራ ተገልጧል፡፡
ከዚህ በፊት ክለቡ ጉዋንዙ ኤቨርግራንዴ 60 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ የሚችል ስታዲየም እንደነበረዉና አሁን የሚገነባዉ ስታዲም ሲጠናቀቅ አንድ መቶ ሺህ ሰዎችን በማስተናገድ 99፣354 ሰዎችን የሚይዘዉን የባርሴሎናዉን ኑ ካምፕ በመብለጥ በዓለማችን በግዙፍነቱ ቀዳሚዉን ቦታ እንደሚይዝ ይጠበቃል፡፡
ስታዲየሙ 16 እጅግ ቅንጡ የግል የእንግዳ ማረፊያዎች 152 ዘመናዊ የግል ማረፊያ ክፍሎች፤ የፊፋ መገልገያ ክፍል፤ የመገናኛ ብዙሃን ክፍል፤ አንዲሁም የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሎችን የያዘ ነዉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ ከ80 ሺህ እስከ 100 ሺህ መያዝ የሚችሉ ሌሎች ለጨማሪ ስታዲየሞችን በተለያዩ የቻይና ግዛቶች በመገንባት በሀገሪቱ ያለዉን የስፖርት ማዘዉተሪያዎች እጥረት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ዘገባዉ አስነብቧል፡፡
ጉዋንዙ ኤቨር ግራንዴ በቻይናና በመላዉ ኤዢያ በእግር ኳሱ ዉጤታማ ከሚባሉ ክለቦች ዉስጥ ተጠቃሽ ሲሆን የሀገሪቱን ከፍተኛ ሊግ ስድስት ጊዜ፤ የኤዢያን ቻምፒዮንስ ሊግ ደግሞ ሁለት ጊዜ ዋንጫ በማንሳት የመጀመሪያዉ የቻይና ክለብ ሆነፐ ተመዝግቧል፡፡